Tender Detail

Tender Details

  • Company የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline07 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 1500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 10,000 (CPO)
  • opening dateበዕለቱ 4:30 ሰዓት
  • Sector House and Building , House and Building Rent

የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ገቢን ለማዘመንና የማዘጋጃ ቤቱን የገቢ አቅም ለማሳደግ የተገነቡትን በአዲስ ገበያ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ 99 (ዘጠና ዘጠኝ) ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የሱቅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ገቢን ለማዘመንና የማዘጋጃ ቤቱን የገቢ አቅም ለማሳደግ የተገነቡትን በአዲስ ገበያ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ 99 (ዘጠና ዘጠኝ) ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል!!
ተጫራቾች:

  1. ለጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ 10,000/አስር ሺ/ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. ለመወዳደር በተፈቀደ የሱቅ ዘርፍ ብቻ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ወይም የንግድ ፍቃድ ለማውጣት ፍቃደኛ የሆኑ፤
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ከአርባ ምንጭ ከተማ ንግድ ገበያ መምሪያ ያወጣ እና ለማውጣት ፍቃደኛ የሆነ ፤
  4. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 1500 ብር ክፍሎ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ይዞ መቅረብ በአ/ምንጭ ከተማ ፋይናንስ ፣ፕላንና ልማት መምሪያ ደረሰኝ በመቁረጥ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ገዝተው በመመልከት መወዳደር ይችላሉ፤
  5. የጨረታው ሳጥን ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ይከፈታል ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ የሚታሸግ ሲሆን በዕለቱ 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፤
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ኦርጅናል የንግድ ፍቃድ ምስክር ወረቀት ኮፒ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ፣ TIN number ወይም የንግድ ፍቃድ ለማውጣት ፍቃደኛ የሆኑበትን ማመልከቻ
  7. አንድ ተጫራች የሱቁን አንድ ካሬ የሚገዛለትን ዋጋ የምይዝ ሰነድ አያይዞ ማቅረብ አለባቸው ከላይ በተ.ቁ 6የተገለፀ መረጃዎችን ፤ ፋይዳ መታወቂያ እና ለጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ ጋር በሰም በታሸገ እንቨሎፕ በከተማ ፋይናንስ፣ ፕላንና ልማት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ያስፈልጋል፤
  8. አንድ ተጫራች ከአንድ ሱቅ በላይ መጫረት አይችልም። ተጫርቶ ከተገኘም ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ይሰረዛል።
  9. ጨረታው የሚዳኘው በዚህ ማስታወቂያና በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀ መመሪያዎች መሠረት ነው።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ:- ተጫራቾች በአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ንግድ ዘርፍ ከገቡት ውል ወጪ የሆኑ ማለትም:- የምግብ ዝግጅት(ሆቴል ሬስቶራንት ካፌና ሻይ ቡና የመሳሰሉት)፤ ስቶር፤ፑል ቤት ቢንጎ/ቁማር/ቤት፤ዳቦ መጋገሪያ፤እንጀራ መጋገሪያ፤የፀጉር ቤት(የወንድም ሆነ የሴት) ማቅረብ ተቀባይነት አይኖረውም:

የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት

Summary
Arba Minch City Municipality invites bids to rent 99 newly built commercial shops at its new market; uses such as food preparation, stores, pool and bingo houses, bakeries and hair salons are excluded.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender