Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
  • Address ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116733497
  • Website
  • Deadline04 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2% (C.P.O ወይም ባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም 4:45፣ ቢሮ ቁጥር 106
  • Sector Packaging, Wrapping and Paper

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የአዲስ ሻይ ቅጠል ነጠላ እና ድርብ ፓኬት ለሻይ ማሸጊያ አገልግሎት የሚውል ወረቀት ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EAC 004/2019

  1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የአዲስ ሻይ ቅጠል ነጠላ እና ድርብ ፓኬት ለሻይ ማሸጊያ አገልግሎት የሚውል ወረቀት ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 - 6:30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 -11:00 ድረስ "ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ" ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ በኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት :-
    • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጎ
    • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጎ እንዲሁም፣
    • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
    • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የአዲስ ሻይ ቅጠል ነጠላ እና ድርብ ፓኬት ለሻይ ማሸጊያ አገልግሎት የሚውል ወረቀት ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (Unconditional) ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ላይ ተጫረ ቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል::
  6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጸለን።
  7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116676204 ፋክስ ቁጥር 0116732006 መጠቀም ይችላሉ።
  8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር

Summary
Ethio Agri-CEFT PLC (MIDROC) invites open bids to supply paper used for packing Addis tea in single and double packets.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender