Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጭሮ ሪጅን
  • Address Oromia Ethiopia, Phone: 251-255-514-044
  • Website
  • Deadline07 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 35,000.00 (CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበዚሁ ቀን 8:30
  • Sector Textile, Leather and Garment , Clothes and Shoes

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጭሮ ሪጅን የሠራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጭሮ ሪጅን

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጭሮሪ /ኤ/አ/ ግ/ጨ/002/2019

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጭሮ ሪጅን ጽ/ቤት በያዘው በጀት ዓመት ለሪጅኑ ሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም

በዚህ ጨረታ ላይ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና፣በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ https://epg.ppa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEU-ጭሮ ሪጅን AACC. (1000254429507) ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ በመያዝ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጭሮ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ፣ ግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 303 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ EEU Chiro Region ተከፋይ የሆነ ብር 35,000.00/ሰላሳ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ቴክኒካል ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ እንዲሁም ፋይናንሻል ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በማድረግ ሲፒኦ/CPO/ኦሪጅናል ቴክኒካል ሰነድ ውስጥ በመክተት አራቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ጭሮ ሪጅን ሐረርጌ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው ህንፃ እራሱ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጭሮ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎ ት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው ኅዳር 28 ቀን 2019 ዓ.ም 8:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል።
  6. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-45-59-57-39 መጠየቅ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጭሮ ሪጅን

Summary
Ethiopian Electric Utility Chiro Region invites bids for tailoring staff uniforms. Bidders must be registered on the public procurement e-GP supplier list.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender