Tender Detail

Tender Details


የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የጽሕፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃ፣ ቋሚ እቃዎች፣ ፈርኒቸርና የደንብ ልብስ ግዥ በ5 ሎት ያወጣው ሀገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር ግጨ- 1 ሀ/ከ/አስ/ገ/ን/331/2019)።

የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ሀገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ግጨ- 1 ሀ/ከ/አስ/ገ/ን/331/2019

የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሁሉም ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ፤ሎት 1 የጽ/መሳሪያ ፤ ሎት 2 የፅዳት እቃ ፤ ሎት 3 ቋሚ እቃዎች ፤ሎት 4 የፈርኒቸር እቃዎች ፤ሎት 5 ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸው፤
  3. የታክስ ክሪላንስ ማቅረብ የሚችል
  4. የግዥ መጠኑ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  6. ማንኛውም ተጫራች ኦርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በባለሙያ ማስፈተሽና ማረጋገጥ አለባቸው፤
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤
  8. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፤
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር ማግኘት ይችላሉ፤
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ 2% በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸዉ የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደተጫራቹ ምርጫ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከ73 ቀን ያላነሰ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ አለባቸው፤
  11. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል
  12. ውድድሩ የሚካሄደው በእቃዎች አይነት በሎት ጠቅላላ ድምር ነዉ.
  13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበትከ 15/03/2019 ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፤
  14. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በ11ኛው ቀን በቀን 25/03/2019 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል።
  15. በጨረታው ለማሳተፍ ለሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር-- ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0921031272 /0938391579 ማግኘት ይችላሉ።
  16. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፉትን እቃ በሀርቡ ከተማ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው።
  17. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ድምር ካላስቀመጡ ከውድድር ውጭ ይደረጋሉ
  18. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ላይ የአንድ ዋጋም ጠቅላላ ዋጋም ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል ።
  19. ተጫራቾች የጨረታ መመሪያ፣የተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ እና የግምገማ ዘዴና መስፈርት በሶፍት ኮፒ መውሰድ ይችላሉ
  20. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

Summary
Harbu Town Administration Finance Office (Amhara) buys goods for all town offices in 5 lots: stationery, cleaning items, fixed assets, furniture and uniforms. Licensed suppliers with TIN and tax clearance may bid; VAT is required above 500,000 birr.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender