Tender Detail

Tender Details


ኦሮ-አሴምብል ግሩፕ የኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ተሽከርካሪ ግዥ

ኦሮ-አሴምብል ግሩፕ

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

ኦሮ-አሴምብል ግሩፕ የ2024/25 ምርት የሆኑትን አውቶሞቢል (Automobile Electrical car) ተሽከርካሪ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ።

  1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  2. በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ፤የተሽከርካሪ አስመጪነት ወይም አምራችነት ፍቃድ ያለው እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  3. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 8ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:00 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ከብ ማህተም በማድረግ እና በመፈረም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋጋዉ 10% ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  6. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ራሳቸዉን ከጨረታ ማግለል አይችሉም።
  8. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተረሰ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  9. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለዉም።
  10. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ዉል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል።
  11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8:30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  12. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ፤ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ :- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 8ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911918329

ኦሮ-አሴምብል ግሩፕ

Summary
Oro-Assemble Group invites licensed vehicle importers or manufacturers to bid for the supply of recent-model electric automobiles. Open bid.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender