Tender Detail

Tender Details

  • Company የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ፣ ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ 19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ፣ 4ኛ ፎቅ ቢሮ 12, Phone:
  • Website
  • Deadline04 Dec 2026, 4:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price250(ሁለት መቶ ሀምሳ ብር)
  • Bid Securityብር 20,852.00 CPO
  • opening dateበአስራ አንደኛው ቀን 3:30 ሰዓት
  • Sector Food and Beverage , Cafe and Restaurant

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት የሰራተኛ ካፌ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 004/2019)።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 004/2019

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1.ሎት 01 የሠራተኛ ካፌ መስተንግዶ

መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢነት ሊስት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የሚወዳደሩት በሚያመርቱ እቃ ወይም ተጨማሪ እሴት ለጨመሩት እቃ ሲሆን ከዚህ ውጭ ለሆኑ እቃዎች የሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና ሲፒኦ(cpo)በማስያዝ ይሆናል። ተወዳዳሪዎች በሚያመርቱት እቃ ሲወዳደሩ እና ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ሲያመጡ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
  • የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የ ተሟላ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታ ሰነዱን በጉለሌ ክ/ከተማ ከወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት ሰነዱን በማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 250 ( ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ። የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
  • ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል።
  • ጨረታው በአስረኛው ቀን 10:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 3:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል።
  • ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጡት ሰነድ ተቀባይነት የለውም። መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማሲያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም ሎት 01 የካፌ መስተንግዶ የሚሆን ብር 20,852.00 ( ሀያ ሺህ ስምንት መቶ ሀምሳ ሁለት ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች በአማራጭ ገበያ መጠቀም የተከለከለ ነው ።
  • ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳ ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት የአሸነፉበትን ዋጋ መጠን እና ብዛት 25% ተጨማሪ ትዕዛዝ መጠየቅ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት።
  • መ/ቤቱ ከውል በፊት እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚችል መታወቅ አለበት።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
አድራሻ፡- ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ 19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Summary
Gulele Sub-City Woreda 2 Finance Office (Addis Ababa) tenders staff cafeteria catering services. Licensed, VAT-registered suppliers on the government supplier list may bid; micro and small enterprises get special support.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender