የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ብርሃን ሪጅን የአንኮበር እና የመሃል ሜዳ የቢሮ መገልገያ አ/መ/ማ አጥር ስራዎችን በ2 ሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር ኢ/ኤ/አገ/ደብ/ሪ/ግጨ/002/2018)።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ብርሃን ሪጅን
የአንኮበር እና መሃል ሜዳ አጥር ስራዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አዝ/ደብ/ሪ/ግጨ/002/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ብርሃን ሪጅን ጽ/ቤት ከዚህ በታች ያሉትን ሁለት አ/መ/ማ/አጥር ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
| ሎት | የቢሮ መገልገያ እቃዎች | የጨረታ ዋስትና | የሚዘጋበት ቀን | የሚከፈትበት ቀን |
|---|---|---|---|---|
| ሎት 1 | የአንኮበር አ/መ/ማ አጥር ስራዎች | 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ብቻ/ | ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት | ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት |
| ሎት 2 | የመሃል ሜዳ አ/መ/ማ አጥር ስራዎች | 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ብቻ/ | ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት | ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ደብረ ብርሃን ሪጅን አፄ-ዘርዓያዕቆብ ህንፃ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ብርሃን ሪጅን ስፓላይ ቼይን ማኔጅመንት ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 306 የማይመለስ ብር 2000.00(ሁለት ሺ ብር ብቻ ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /cpo/ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ህዳር 22/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ስፓላይ ቼይን ማኔጅመንት ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 306 የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond)ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሳምፕል የማቅረብ፣ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካል «ኦሪጅናል እና ኮፒ » እና ፋይናንሻል «ኦሪጅናል እና ኮፒ » በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አገ/ደብ/ሪ/ግጨ/002/2019 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ህዳር 22/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 306 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከ 8:30 ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-637-60-94 መደወል ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደብረ ብርሃን ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
Summary
Ethiopian Electric Utility, Debre Birhan Region, tenders fence construction works in 2 lots: Ankober and Mehal Meda. Licensed contractors with VAT, TIN and public procurement registration may bid.
