የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር 03/2019)።
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2019
በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የስፖርት ምክር ቤት ግዥ ቡድን በግልፅ ጨረታ ቁጥር 03/2019 ዓ.ም ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት1. የተለያዩ የስፖርት የትጥቅ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመቅረብ ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች:- ሀ. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ለ. የተጨማሪ እሴት ታስክ የተመዘገበ ፣ታክስ ክሊራንስ እና ቲን ነበር ማቅረብ የሚችል።
- በየሎቱ በተቀመጠው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን (CPO) "የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት " በሚል ስም በማሰራት ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ የተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ለጨረታ ከቀረቡት አገልግሎቶች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ 25 ጨምሮም ሆነ ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው ቢያሸንፉ ሊያቀርቡ የሚችሉትን አገልግሎቶች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልፆ በሚሰጠው የግዥ ትዕዛዝ መሠረት አገልግሎቶችን ቀደም ሲል አቅርቦት በተመረጠው ናሙና መሠረት ለመ/ቤታችን ለማቅረብ አለበት።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10:30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0118722106 አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አጠገብ ወይም በላይ ተከሉ ኬክ ቤት አጠገብ 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት
Summary
Lideta Sub-City Sport Council (Addis Ababa) buys various sports kits and sportswear by open tender. Licensed suppliers with VAT, TIN and tax clearance may bid; samples must be submitted before the tender closes.
