Tender Detail

Tender Details


በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የድሬ ዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለጥገናና ለስልጠና ግብዓት የሚውሉ ብረታ ብረትና እንጨት ስራ ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሣሪያ፣ የፅዳትና ቋሚ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክና አውቶመካኒክ፣ የልብስ ስፌት ስልጠናና የደንብ ልብስ ጨርቃ ጨርቅና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የድሬዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የድሬ ዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጥገናና የስልጠና ግብዓት ለብረታ ብረትና እንጨት ስራ፣ የፅህፈት መሣሪያ፣ ለፅዳትና ለከፊል ቋሚ ዕቃዎች ለኤሌክትሪክና ለአዉቶመካኒክ ሥልጠና፣ለልብስ ስፌት ሥራ ስልጠና እና ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚዉሉ ጨርቃ ጨርቅና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች:-

ከላይ የተገለፁትን ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ መደረጉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች፣የዕቃ(የአገልግሎት) አቅራቢዎች ምዝገባ ስለመታቀፋቸዉ ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጣቸውን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም ከግዥ ኤጀንሲ በተለቀቀ የመረጃ መረብ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ እንዲሁም የሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ህጋዊ ማስረጃዎችን ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባችኋል።

ስለሆነም :-

  1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት የቴክኒክና የዋጋዉ ሰነድ በአንድ ኢንቨሎፕ በማድረግና በማሸግ በግልፅ በፖስታዉ ላይ በመፃፍና በመፈረም ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ በታሸገዉ ፖስታ ማስገባት አለባቸዉ።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አስር) ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት በድሬ ዳዋ ማ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 311 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን፣ጨረታዉ የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በተመለከተ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን በጨረታ ሰነድ ዉስጥ ያገኙታል።
  5. ተጫራቾች ሰነዶችን ለማስገባት ሲመጡ ስለሚጫረቱባቸዉ የዕቃዎች ናሙና አብረዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም የቴክኒካልና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነዱ በመ/ቤታችን በተባለው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የድሬ ዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት ድሬ ዳዋ

Summary
Dire Dawa Correctional and Remand Centre (Federal Prisons Commission) buys metalwork and woodwork, stationery, cleaning and furniture items, electrical and auto-mechanic training inputs, tailoring training materials and uniform fabrics. Licensed, VAT-registered suppliers may bid.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender