የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት፣ የፅዳት፣ የኤሌክትሪክ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ፣ የቧንቧ ዕቃዎች፣ የግንባታ ማቴሪያል፣ ደንብ ልብስ፣ የኦክስጅን ፕላንት ጥገና፣ የአሉሚኒየምና ጣውላ ፈርኒቸር ስራ፣ የህሙማን አልባሳት አጠባና የኤሌክትሮኒክስ ጥገናን በ13 ሎቶች በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር 2118/2019)።
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:2118/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ፥ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ሎት 3 ኤሌክትሪክ እቃዎች ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፥ ሎት 5 ቋሚ እቃዎች ፥ሎት 6 የቧንቧ እቃዎች ፥ሎት 7 ግንባታ ማቴሪያል ፥ሎት 8 የደንብ ልብስ ግዥ ፥ ሎት 9 የኦክስጂን ፕላንት እና የውሀ ትሪትመንት ፕላንት ጥገና ፥ ሎት10 የአልሙኔየም ብረታብረት ስራ ለአንድ ጊዜ ብቻ ለማሰራት ፥ ሎት 11 ጣውላና ፈርኒቸር ስራ ለአንድ ጊዜ ብቻ ፥ ሎት 12 ተኝተው ለሚታከሙ የህሙማን አልባሳትና የባለሞያዎች አልባሳት አጠባ ለአንድ ዓመት አገልግሎት የሚውል ፥ ሎት 13 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ለአንድ ዓመት አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ ለማሰራት/ ይፈልጋል።
ስለሆነም አግባብነት ያላቸውን ሁሉ በጨረታው እየጋበዝን
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአቅርቦትና የአገልግሎት አይነት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን-ነበር ማቅረብ የሚችሉ
- ኤክሳይዝ ታክስ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥው ወይም የአገልግሎቱ መጠን ከ 500,000.00 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-5 የተገለፁትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ለእንዳንዱ ሰነድ በሚነበብ መልኩ ኮፒ በማድረግ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቃል።
- ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ከሆስፒታሉ ግዥ ክፍል የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ በቁርጥ ሰነዱ ላይ በሚቀመጠው የብር መጠን ሲፒኦ በማዘጋጀት / በማሲያዝ/ ከኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል የጨረታ በሚያስገቡበት ጊዜ ዋናው የጨረታ ሰነድ እና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታ በማሸግ እንደገና ሁለቱንም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ በጥንቃቄ በሰም በማሸግ የድርጅቱ ስም አድራሻውና ማህተም በመምተታ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በማስታወቂያ በወጣበት 10 ተከታታይ በመጨረሻ በ11ኛ የስራ ቀን ከረፋዱ 4:00 ታሽጎ በእለቱ 4:30 ይከፈታል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ነው።
- ሆስፒታሉ ቫት (7.5) እና ዊዝ ሆልድ (3%) ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን ይታወቅ።
- ሆስፒታሉ በሚጋብዛቸው የቴክኒክ ባለሙያ ተረጋግጦ እቃው አገልግሎቱ /ገቢ ይሆናል።
- ሆስፒታሉ በሚያቀርበው ናሙና እቃው ገቢ ይሆናል።
- የአገልግሎት ዘመን ያላቸው እቃዎች ቢያንስ ከአንድ አመት በላይ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- አስፈላጊ መረጃ መስጠት ከፈለጉ በሆስፒታሉ ስልክ ቁጥር 0331117670 መደወል ይችላሉ።
ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
Summary
Dessie Comprehensive Specialized Hospital buys in 13 lots: stationery, cleaning, electrical, electronics, furniture and plumbing items, building materials and uniforms, plus oxygen and water plant repair, aluminium and wood works, laundry, and electronics repair.
