የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት በቦንጋ ከተማ ከ12 እስከ 14 ክፍል ወይም ከ150 እስከ 250 ካ.ሜ የሆነ የቢሮ ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ያወጣው ማስታወቂያ።
በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕ/ሪጅን ቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኛ ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕ/ሪጅን ለቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚትችሉ ሙኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም:-
- ከ12 እስከ 14 ክፍል ወይም ከ150 እስከ 250 ካሬ ሜትር ሆኖ የክፍሎቹ ስፋት ቢያንስ 3×3m2 እና ከዚህ በላይ ሆኖ ከዚህ ውስጥ ብያንስ 5(አምስት) ክፍል ስፋቱ 5×6m2 እና ከዚህ በላይ
- ቤቱ ሙሃ፣ መብራትና መጸዳጃ ቤት ኖሮት ሕንፃ ከሆነ መነሻው G+0 ሆኖ መጨረሻው ከ G+2 በላይ ያልሆነ ሲሆን ከቦንጋ ከተማ ይሄንን ማሟላት የሚችል ህንጸ ያላችሁ ባለንብረቶች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- ከቦንጋ ከተማ መሐል አደባባይ ጀምሮ በገ/ጻዲቅ ሻዎ ሆስፒታል አቋርጦ በሚመጣው አስፓልት መንገድ ይዞ እስከ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቢሮ ድረስ ከዋና አስፓልት እስከ 100 ሜትር ግራ እና ቀኝ ገባ ብሎ
- ከቦንጋ ከተማ መሐል አደባባይ እስከ ኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ከዋና አስፓልት እስከ 100 ሜትር ግራ እና ቀኝ ገባ ብሎ
- ከቦንጋ ከተማ መሐል አደባባይ እስከ መስጊድ (ዴቻ መመለሻ) ከዋና አስፓልት እስከ 100 ሜትር ግራ እና ቀኝ ገባ ብሎ መወዳደር እንደሚችሉ እና ተወዳዳሪዎችም:-
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ፣ የቫት ሠርተፍኬቱን ኮፒ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የምትሰጡት ዋጋ ቫትን ማካተቱና ያለማካተቱን መግለጽ ያለባቸው ሆኖ ይሄ ሳይገለጽ ከቀረ ያቀረቡትን ዋጋ ቫትን ያካተተ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተወዳዳሮች ቤቱ ሕጋዊ ስለመሆኑ ወቅታዊ ግብር የከፈሉበት ሕጋዊ ደረሰኝ እና የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር/ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2:00 እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ በደቡብ ምዕራብ ሪጅን ቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመግዛትና የሚያከራዩበትን የአንድ ወር ዋጋ በመሙላትና በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከሰዓት በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕ/ሪጅን ቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር :-0473312643
በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕ/ሪጅን ቦንጋ ቅ/ጽ/ቤት
Summary
Public Servants Social Security Administration, South West Region Bonga branch, seeks to rent an office building in central Bonga: 12 to 14 rooms or 150 to 250 sq m, G+0 to G+2, with water, power and toilets. Owners of legal buildings with paid taxes may bid.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
