የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ መገናኛ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ መዋቢያዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የምግብ ነክ ዕቃዎች፣ የመኪናና የሞተር ሳይክል አካላት በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ በግልፅና ሀራጅ ጨረታ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር 16/2019)።
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 16/2019
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ እና ሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች (ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ጥራቱን በጠበቀ ስካን በማድረግ ኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው ጊዜ መሰረት በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ኦንላይን በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5 % (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለት C.P.O ለእያንዳንዱ ኮድ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ ቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ወይም ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በአካል በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው ቀን ድረስ ዕቃዎቹን ናሙና ወይም ንብረቶቹን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን የግልጽ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው ቀን ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ ይዘጋል።
- የሀራጅ ጨረታው በተመሳሳይ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ተጀምሮ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ 6:00 የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ። በዚህ ጨረታ ለቀረቡት እቃዎች ተጫራቾች የሚሰጡት የሀራጅ ጨረታ ማሸነፊያ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ን ያካተተ ሲሆን ለእያንዳንዱ ኮድ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል (ለኮድ 01 ብር 33,000፤ ለኮድ 02 ብር 118,000፤ ለኮድ 03 ብር 31000፤ ለኮድ 04 ብር 29,000፤ ለኮድ 05 ብር 55,000፤ ለኮድ 06 ብር 55,000፤ ለኮድ 07 ብር 560,000፤ ለኮድ 08 ብር 88,000፤ ለኮድ 09 ብር 80000፤ ለኮድ 10 ብር 27,000፤ ለኮድ 11 ብር 27,000፤ ለኮድ 12 ብር 8,000፤ ለኮድ 13 ብር 5,000፤ ለኮድ 14 ብር 700፤ ለኮድ 15 ብር 33,000፤ ለኮድ 16 ብር 76,000፤ ለኮድ 17 ብር 6000፤ ለኮድ 18 ብር 140000፤ ለኮድ 19 ብር 55000፤ ለኮድ 20 ብር 34,000፤ ለኮድ 21 ብር 32,000 እና ለኮድ 22 ብር 40,000)።
- ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች፣ በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት (3) ቀናት የሚመለስላቸው ይሆናል።
- ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ በተለጠፈው ፎቶ ብቻ ተመልክተው ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚጭኑት/የሚያቀርቡት ሰነድ ጥራቱን በጠበቀ መሳሪያ ስካን የተደረገ እና አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ብቻ እንዲያቀርቡ ይመረጣል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎችን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ:- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕስቶር ወይም ፕሊይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ 09-05-11-55-11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
ለበለጠ መረጃ የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ሥራ ሂደት የስልክ ቁጥር:- 046-212-53-96 / 046-220-1936 ይደውሉ
የቴሌግራም ግሩፕ:-https://t.me/hawassaaweqaged
