አድዋ ድል ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የተቋሙን ፋይናንሻልና ሌሎች ሰነዶች ለሶስት ዓመት የውጭ ኦዲት (External Audit) ለማሰራት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ያወጣው ማስታወቂያ (አ/ድ/ማ/ፋ/ብ/ግ/ጨ-02/2019)።
Adwa Dil Microfinance Institution S. C
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- አ/ድ/ማ/ፋ/ብ/ግ/ጨ-02/2019
አድዋ ድል ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለተለያዩ ዓይነት የተቋሙ ፋይናንሻልና ሌሎች ሰነዶችን EXTERNAL AUDIT በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ለሶስት ዓመት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች:-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ፤ የተእታ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ፤ የታክስ ከፋይ መለያ ቲን እና ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡበት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበ ሰነድ ቅደም ተከተል መሰረት ቫትን ጨምሮ ነው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አጠቃላይ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን በአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በሚል ባንክ ጋራንቲ ቦንድ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ(ሲፒኦ) ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ በፍፁም የተከለከለ ነው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለያይተው ማቅረብ አለባቸው ይሄ ካልሆነ ያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ብቁ የሚሆነው በዝርዝር የተቀመጠውን የጨረታ መመሪያ ሲያሟላና በጨረታ መመሪያ መሰረት ሲያቀርብ ነው። የጨረታ መመሪያ ያላሟላ ተጫራች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ) አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በሚል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000735396912 በማስገባት ኦሪጂናል ደረሰኝ ብቻ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ጦር ኃይሎች አካባቢ ሙሉ ወንጌል ቸርች ወረድ ብሎ አላ ማደያ አጠገብ መውሰድና ማየት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በNOVEMBER 23/2026 ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር 7:30 ሰዓት ታሽጎ በ8:00 ሰዓት ይከፈታል ዕለቱ ሰንበት ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
- አድራሻ ቦታ ጦር ኃይሎች አካባቢ ሙሉ ወንጌል ቸርች ወረድ ብሎ አላ ማደያ አጠገብ ግዥ ክፍል ሲሆን ስልክ ቁጥር:- 011-3-85-16-13 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል።
- አክሲዮን ማህበሩ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Adwa Dil Microfinance Institution S.C. seeks an external audit firm to audit its financial and other records for three years through national open bidding. Bidders need a renewed licence, VAT, TIN and accreditation from the Accounting and Auditing Board of Ethiopia.
