Tender Detail

Tender Details

  • Company አብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ባህርዳር
  • Address , Phone: 0582220132
  • Website
  • Deadline16 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price1000(አንድ ሺህ ብር)
  • Bid Security1,500,000.00 ብር በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ስም
  • opening dateበዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል።
  • Categories Construction and Water Works , Water Construction , Water System Installation

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ በሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ የአስታይሽ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የግንባታ፣ የቧንቧ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ሥራ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለማሰራት ያወጣው ማስታወቂያ (አብክመ/ውኢቢ/ብግጨ/ግስግ/ቁጥር-01/2019)።

አብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ባህርዳር


የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ
የሥራው ዓይነት:- ለአስታይሽ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ የቧንቧ፣ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ስራ
የታተመው ህዳር 07 2019 ዓ.ም
የግዥው መለያ ቁጥር:- አብክመ/ውኢቢ/ብግጨ /ግስግ/ቁጥር-01/2019
የግዥ ዘዴ፤ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለአስታይሽ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት በተመደበው በጀት መሠረት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም መስፈርቱን የሚያሟሉ በውሃ ነክ ሥራዎች ተቋራጭነት ፈቃድ ያላቸው ተቋራጮች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። ስለዚህ ብቁ የሆናችሁ ተጫራቾች በሙሉ በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።

ተ.ቁየፕሮጀክቱ ስምወረዳዞንፕሮጀክቱ ዓይነትየጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር
1አስታይሽ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክትጋዞበሰ/ወሎግንባታ፣ የቧንቧ፣ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ስራ1,500,000.00

በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል:-

  1. በውሃ ነክ ሥራዎች ተቋራጭነት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት /ሰርቲፊኬት/ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  2. በዘመኑ የታደሰ እና ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከቢሮው ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 23 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከዚህ በላይ በተመለከተው ሰንጠረዥ መሠረት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች ማለትም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ (Amhara National Regional State Bureau of Water and Energy) ስም የተዘጋጀ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች ፋይናንሻል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች በማሸግ በድምሩ ስድስት ለየብቻ በታሸገ ፖስታዎች እና ቴክኒካል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች የታሸጉ ፖስታዎች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በፖስታ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ ፋይናንሻል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች ፖስታዎችን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ፊርማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ሎት የግዢውን ስም በመጻፍ በውኃና ኢነርጂ ቢሮ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. የስርዝ ድልዝ ወይም የተፋቀ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  9. ጨረታው መዝጊያ ቀን 07/04/2019 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን በዚሁ ቀን ጨረታው 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል። የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በቀጣዩ የስራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በዚህ ግዥ ላይ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 ላይ የተቀመጡት መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
  12. ለተጨማሪ መረጃ በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥሮች +251582-26-24-60/+251582-20-08-55/ በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር +251582-26-24-61 በመላክ ወይም ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት

ውኃና ኢነርጂ ቢሮ
ባሕር ዳር

✨ messages.ai_summary
The Amhara Region Water and Energy Bureau seeks licensed water-works contractors to build the Astayish town drinking water project in Gazo Woreda, North Wollo, including pipes, fittings and electromechanical supply and installation.
Save Tender