የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ የወይን ውኃ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የግንባታ፣ የቧንቧ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ሥራ (Packed System) በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለማሰራት ያወጣው ማስታወቂያ (አብክመ/ውኢቢ/ብግጨ/ግስግ/ቁጥር-02/2019)።
አብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ባህርዳር
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ
የሥራው ዓይነት- ወይን ውኃ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ የቧንቧ፣ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ሥራ (Packed System)
የታተመው፤ ኅዳር 7/2019
የግዥው መለያ ቁጥር- አብክመ/ውኢቢ/ብግጨ/ግስግ/ቁጥር-02/2019
የግዥ ዘዴ፤ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ወይን ውኃ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት (Packed System) በተመደበው በጀት መሠረት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም መስፈርቱን የሚያሟሉ በውሃ ነክ ሥራዎች ተቋራጭነት ፈቃድ ያላቸው ተቋራጮች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። ስለዚህ ብቁ የሆናችሁ ተጫራቾች በሙሉ በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።
| ተ.ቁ | የፕሮጀክቱ ስም | ወረዳ | ዞን | ፕሮጀክቱ ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር |
|---|---|---|---|---|---|
| 1 | ወይን ውኃ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት (Packed System) | ቢቡኝ | ምስ/ጎጃም | ግንባታ፣ የቧንቧ፣ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ሥራ (Packed System) | 1,800,000.00 |
በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል:-
- በውሃ ነክ ሥራዎች ተቋራጭነት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት /ሰርቲፊኬት/ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- በዘመኑ የታደሰ እና ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከቢሮው ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 23 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከዚህ በላይ በተመለከተው ሰንጠረዥ መሠረት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች ማለትም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ (Amhara National Regional State Bureau of Water and Energy) ስም የተዘጋጀ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች ፋይናንሻል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች በማሸግ በድምሩ ስድስት ለየብቻ በታሸገ ፖስታዎች እና ቴክኒካል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች የታሸጉ ፖስታዎች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በፖስታ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ ፋይናንሻል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች ፖስታዎችን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ፊርማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ሎት የግዢውን ስም በመጻፍ በውኃና ኢነርጂ ቢሮ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የስርዝ ድልዝ ወይም የተፋቀ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው መዝጊያ ቀን 07/4/2019 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን በዚሁ ቀን ጨረታው 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል። የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በቀጣዩ የስራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በዚህ ግዥ ላይ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 ላይ የተቀመጡት መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
- ለተጨማሪ መረጃ በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥሮች +251582-26-24-60/+251582-20-08-55/ በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር +251582-26-24-61 በመላክ ወይም ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት
ውኃና ኢነርጂ ቢሮ
ባሕር ዳር
✨ messages.ai_summary
The Amhara Region Water and Energy Bureau seeks licensed water-works contractors to build the Wayen Wuha town drinking water project (packed system) in Bibugn Woreda, East Gojjam, including pipes, fittings and electromechanical supply and installation.
