Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address መ/አምባ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113360162
  • Website
  • Deadline04 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 300 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 70,000 (CPO፣ ለ90 ቀናት)
  • opening dateበዚያኑ ቀን በ8:30 ሰዓት
  • Categories Building Construction , Renovation

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የእንስሳት ጤና ኬላ ግንባታና የጤና ኬላ ጥገና ስራ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/0007/2019

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው በግብርና ጽ/ቤት አማካይነት ለሚያሰራው የቀቻ ቀበሌ አዲስ የእንስሳት ጤና ኬላ ግንባታና ጅማ ከተማ ጤና ኬላ ጥገና ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

  1. የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC / BC ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች።
  3. ከገቢዎች መስሪያ ቤት የኦዲት ክሊራንስ ማምጣት የሚችሉ።
  4. ተወዳዳሪዎች የቫት 7.5% ተቀናሽ ለማድርግ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።
  5. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 8:00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  7. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ብር 70000 (ሰባ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20(ሀያ) ተከታታይ የስራ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በ8:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።

ማሳሰቢያ:-

  1. በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
  2. በወረዳው ወስጥ አንድም ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም።
  3. ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
  5. አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ክፍያ ሳይወስድ/ሳይጠይቅ ስራ መጀመር የሚችል።

ለበለጠ መረጃ:- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልክ ቁጥር 0113360162/146 ይደውሉ
መሀል አምባ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Gedebano Gutazer Wolene Woreda Finance Office (Gurage Zone) invites GC/BC grade 8 and above contractors to build a new animal health post in Yeqecha kebele and renovate the Jima town health post. National open bid.
Save Tender