Tender Detail

Tender Details


የደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት የቧንቧ፣ ኤሌክትሮ መካኒካል፣ ኮምፒውተር፣ ክሎሪን፣ የጽህፈት መሳሪያ ግዥና የውሃ ሞተር ፓምፕ ጥቅል ስራ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር የደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1.የቧንቧ እና መገጣጠሚያዎች ሎት 2.የሲዊች ቦርድ ከነ ሙሉ አክሰሰሪውና ኤሌክትሮ መካኒካልእቃዎች ሎት 3.የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች ሎት 4.የክሎሪን ዱቄት ሎት 5.የጽ/መሳሪያዎች ግዥ ሎት 6 የውሃ ሞተር ፓምፕ ማስጠቅለል በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት እና ማስጠቅለል ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር / TIN / ያላቸው ፤
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
  4. የሚገዙ እቃዎችን እና የሚጠቀለለው የውሃ ሞተር ፓምፕ አይነት እና ዝርዝር መግለጫ / Specification / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይቻላል::
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት የዕቃውን 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በአንድ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና አድራሻቸውን በመሙላት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ድረስ ደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ላይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ እና የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት ከጠ[...]ቱ 3:30 ላይ ተዘግቶ / ታሽጎ / ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:00 ላይ ደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 የሚከፈት ሆኖ 16ኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል: ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ::
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚያዝበት ወቅት ያሸነፈበትን ዕቃ ዋጋ 10% የውል ማከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / CPO / ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፊበትን ዕቃ /ንብረት / ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን ደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል::
  10. ውድድሩ በነጠላ ወይም በጥቅል ዋጋ / ሎት/ ይሆናል::
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ከገቢ ግ/ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0587761715 /0587760015 /በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል::

የደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት

Summary
Dejen Town Water Service Office (East Gojjam, Amhara) seeks suppliers in 6 lots: pipes and fittings, switch boards and electro-mechanical items, computers, chlorine powder, stationery, and water motor pump rewinding. Open bid.
Save Tender