Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) (የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን)
  • Address ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ምናዬ ኮርፖሬት ቢሮ ፓርክ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-83-27
  • Websitehttps://ecma.gov.et/
  • Deadline27 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 20,000.00 (የባንክ ዋስትና ወይም CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን ጠዋት በ4:30፣ በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ
  • Categories Safety And Security

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የጥበቃ አገልግሎት ግዥ (Outsourcing Security Services)

Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) (የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- ECMA/NCB/OB/05/2019

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የጥበቃ አገልግሎት ግዥ (Procurement of outsourcing Security Services) በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል:: በዚሁ መሰረት:-

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤታችን የንግድ ባንክ አካውንት 1000586364824 ገቢ በማድረግ ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
  2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ክሊራንስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  4. ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰአት በፊት ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
  5. ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆዩበት ጊዜ ከ90 ቀናት ያላነሰ መሆን አለበት::
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል::
  7. አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት::
  8. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  9. ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
  10. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
  11. ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን ጠዋት በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጠዋት በ4: 30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
  12. በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም::
  13. ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይቻላሉ::

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
ከፍላሚንጎ ሬስቶራንት ወደ አደራ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ምናዬ ህንፃ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ 011-5-57-83-27
ኢሜል: Procurement@ecma.gov.et

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Capital Market Authority seeks licensed firms to provide outsourced security services. National open bid.
Save Tender

ተቋማችን Supply,Delivery, Installation & Commissioning of CCTV Cameras ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

READ MORE
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Supply of External wet type fire hydrant...

READ MORE
Dashen Bank S.C – Supply and Installation of Fire Suppression Systems and 40KW Hybrid Solar Inverter...

READ MORE