ተቋማችን Supply,Delivery, Installation & Commissioning of CCTV Cameras ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ፋፋግ/ግጨ-017/2019
ተቋማችን Supply,Delivery, Installation & Commissioning of CCTV Cameras ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
| ሎት | የዕቃው ዓይነት | የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) | የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
| 1 | Supply, Delivery, Installation & Commissioning of CCTV Cameras ግዥ | 100,000.00 | ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት | ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ ይችላል::
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ::
- አድራሻ:- ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል ስልክ ቁጥር 011-156-01-48
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና <<ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY>> በሚል መሆን ይኖርበታል፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል::
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
Summary
Ethiopian Electric Utility invites bids for the supply, delivery, installation and commissioning of CCTV cameras. Open bid.
