Tender Detail

Tender Details

  • Company Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 439 00 75
  • Website
  • Deadline21 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 1000.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት1 ብር 110,200.00፤ ሎት2 ብር 160,000.00፤ ሎት3 ብር 280,000.00 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዚሁ ቀን 4:30 ሰዓት
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant , Vehicle Spare Parts , Battery

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የተሽከርካሪ ባትሪ፣ ቅባቶች፣ ግሪስና ሌሎች ፈሳሾች እና የተለያዩ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የማዕቀፍ ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል::

Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)


ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ለተሽከርካሪ ባትሪ፣ ቅባቶች፣ ግሪስና ሌሎች ፈሳሾች እና የተለያዩ መለዋወጫዎች

በግዥ መለያ ቁጥር: ERTE/ NCB/G/004/2019

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የተሽከርካሪ ባትሪ፣ ቅባቶች፣ ግሪስና ሌሎች ፈሳሾች እና የተለያዩ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የማዕቀፍ ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል::

በዚህም መሠረት በግልፅ ጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ማሟላትና ማቅረብ አለባቸው::

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት፤ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተቀባይነት ያለው የግብር ክሊራንስ (ታክስ ክሊራንስ)፤በአቅራቢነት (EGP) ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ::
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 የተሽከርካሪ ባትሪ ብር 110,200.00 (አንድ መቶ አስር ሺህ ሁለት መቶ ብር) ፤ለሎት 2 የሞተር ዘይት ማጣርያ እና የተለያዩ መለዋወጫዎች ብር 160,000.00 (አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ብር) እና ለሎት (lot) 3፡ የሞተር ዘይት ፤ ግሪስና ሌሎች ፈሳሾች ብር 280,000.00 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) ወይም ህጋዊ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው:: የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለ90 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት::
  3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የፋይናንስ ዲፓርትመንት መግዛት ይችላሉ::
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4:30 ሰዓት ይከፈታል፤ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይሆናል::
  5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

የድርጅቱ የሥራ ሰዓት

  • ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00 ሰዓት - 6:00 ሰዓት
  • ከሰዓት ከ7:00 ሰዓት - 11:00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ እስከ 10:00 ሰዓት

አድራሻ:-
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት አሁን ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር 0114390075/1569/3592/0114391027
ፋክስ 0114-39-63-36 ፖ.ሳ.ቁ. 2562

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Emergency Relief Transport Enterprise seeks suppliers of vehicle batteries, motor oil, grease and other fluids, oil filters and various spare parts in 3 lots under a one-year framework agreement. Open bid.
Save Tender