ፀደይ ባንክ አ.ማ የKaspersky Antivirus License Renewal and Upgrade ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0010/2019 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0010/2019
ፀደይ ባንክ አ.ማ Kaspersky Antivirus License Renewal and Upgrade ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
- የ2018/19 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመካፈል/ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ ጊዜው ያላለፈበት። ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ የሂሳብ ቁጥር 1201390000037 በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው እስከሚዘጋበት ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ውል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በተዘጋበት ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታው መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ስልክ ቁጥር 0115581658
ፀደይ ባንክ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Tsedey Bank S.C. seeks licensed suppliers for Kaspersky antivirus licence renewal and upgrade through an open tender. Bidders need a renewed 2018/19 trade licence, VAT certificate and a valid tax clearance for tender participation.
