የጉራጌ ዞን ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የG+2 ቢሮ ግንባታ ቀሪ ሥራዎች፣ አጥር፣ የጥበቃ ቤት እና ሴፕቲክ ታንክ ግንባታ
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/005/2019
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለወረዳው ት/ት/ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የG+2 ቢሮ ግንባታ ቀሪ ሥራዎችን አጥር የጥበቃ ቤት እና ሴፕቲክ ታንክ ግንባታ ለማሠራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል::
ስለሆነም ተጫራቾች :-
- የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ፣ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ሕጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው :
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8:00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት/ መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሐልአምባ ከተማ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ::
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 4 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች::
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 500000 ( አምስት መቶ ሺህ ብር) ብቻ በገ/ጉ/ወ/ወ/ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 25 (ሃያ አምስት) ተከታታይ ቀናት መሐልአምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር -03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው ሰነድ በ25ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይታሸጋል:: ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- አሰሪው መስሪያቤት ለጨረታው አሸናፊ ድርጅት ቅድመ ክፍያ የማይከፈል መሆኑን እና ሥራው ደግሞ በደረሰበት ታይቶና ተረጋግጦ የደረሰበት ክፍያ የሚፈጸም መሆኑን:
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ :-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም ::
- በወረዳው ውስጥ ፕሮጀክት ይዞ ሥራውን ያልጨረሰ ተጫራች መወዳደር አይችልም ::
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሠሪው መሥሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና መሆን አለባቸው::
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል::
ለበለጠ መረጃ:- ስልክ ቁጥር 0113360162/146 ይደውሉ
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ መሐል አምባ
✨ messages.ai_summary
A woreda finance office in Gurage Zone (Mehal Amba, Central Ethiopia) seeks GC/BC-4 or above contractors to complete a G+2 office building and build a fence, guard house and septic tank. No advance payment; site visit letter required. Open bid.
