Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Orthodox Tewahido Church-Child and Family Affairs Organization Genete Eyesus Child and Family Development Program Coordination Office
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0111142948
  • Website
  • Deadline13 Nov 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Securityተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ 2% በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  • opening dateበዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • Categories Personal Care Products And Services

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የገነተ ኢየሱስ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለተማሪዎች የሚሰጥ የንፅህና መጠበቂያ Rose ሞዴስ 3,100/ሶስት ሺህ አንድ መቶ/ አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Orthodox Tewahido Church-Child and Family Affairs Organization Genete Eyesus Child and Family Development Program Coordination Office


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የገነተ ኢየሱስ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለተማሪዎች የሚሰጥ የንፅህና መጠበቂያ Rose ሞዴስ 3,100/ሶስት ሺህ አንድ መቶ/ አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች:-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚያበቃቸው በሥራ ዘርፉ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ የዘመኑ ንግድ ሥራ ፈቃድ መኖር አለበት
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት መቅረብ አለበት
  3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት መኖር አለበት
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከድርጅታችን መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ 2% በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት 5/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የንፅህና መጠበቂያ Rose ሞዴስ አይነት አንድ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  8. ጨረታውን አሸናፊ ድርጅት ለተማሪዎች የሚሰጥ የንፅህና መጠበቂያ Rose ሞዴስ ውል ከተፈረመበት ዕለት ጀምሮ በ2 /ሁለት/ ቀናት ውስጥ ማስረከብ ይኖርበታል። እንዲሁም በራሱ ትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  9. የሞዴሶቹ ብዛት በሚሰጠው ዋጋ መሰረት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።
  10. ጨረታው ኅዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም. 6:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-14-29-48 መጠየቅ ይቻላል።
  13. CPO የሚሠራበት ስም EOC – CFAO Genete Eyesus Child and Family Development Program Coordination Office በሚል ይሆናል።

አድራሻ በየካ ክ/ከ ወረዳ 1 ከገነተ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ዝቅ ብሎ ወደ ፈረንሣይ ኢምባሲ በሚወስደው መንገድ ሚያዚያ 23 ት/ቤት ሳይደርሱ ከሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የገነተ ኢየሱስ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
EOTC Child and Family Affairs Organization, Genete Eyesus Child and Family Development Program Coordination Office, Addis Ababa, buys 3,100 Rose sanitary pads for students by tender. Bidders need a renewed trade licence in the field, VAT and supplier registration.
Save Tender