Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline23 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityመጠን: 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ወይንም በውጭ ሀገር መገበያያ ገንዘብ (የአሜሪካ ዶላር፣ የእንግሊዝ ፓውንድ፣ ወይም ዩሮ) በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ (Bank Guarantee) ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ::
  • opening dateየጨረታ መክፈቻ: በዕለቱ 4:30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል::
  • Categories Industrial Machinery Provision And Installation , Machinery

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለ2019 በጀት ዓመት ከቅድመ ህትመት እስከ ድህረ ህትመት የሚያገለግሉ የማተሚያ ማሽኖችን (Sheet Fed Offset Press፣ Folding Machine፣ Paper Cutting Machine፣ Perfect Binding Machine፣ Double Saddle Stitcher፣ Laminating Machine፣ Heavy Duty Printer እና Thermal CTP) በዓለም አቀፍ ግልጽ

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


በድጋሚ የወጣ ዓለም አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የማተሚያ ማሽኖችን ከቅድመ ህትመት እስከ ድህረ ህትመት ማለትም

  • sheet fed offset press,
  • folding machine,
  • paper cutting machine,
  • perfect binding machine,
  • double saddle stitcher,
  • laminating machine,
  • heavy duty printer,
  • Thermal ctp በዓለም አቀፍ የግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም:-

1. የብቃት መስፈርቶች

ለሀገር ውስጥ ተጫራቾች:-

  • በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  • የንግድ ምዝገባ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
  • የቫት ሰርተፍኬት
  • በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ
  • በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል በዘመኑ የተሰጠ የግብር ከፍያ ማረጋገጫ ደብዳቤ (Tax Clearance)

ለውጭ ተጫራቾች ደግሞ:-

  • ህጋዊ እና የንግድ ፈቃድ ማረጋገጫዎች
  • በተመዘገቡበት ሀገር ህጋዊ ኩባንያ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የንግድ ምዝገባ ሰነድ
  • በተፈለገው የስራ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችል የታደሰ የንግድ ፈቃድ
  • ተመዝገበበት ሀገር ከሚመለከተው የታክስ ባለስልጣን የተሰጠ ህጋዊ የግብር ከፍያ ማረጋገጫ ሰነድ (Tax Clearance Certificate)
  • Power of Attorney: የድርጅቱ ወኪል ወይም ህጋዊ ተወካይ ጨረታውን ለመፈረምና ለማስገባት የሚያስችለው የተፈረመና የታተመ የውክልና ሰነድ
  • በፌዴራል መንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ

2. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond)

  • መጠን: 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ወይንም በውጭ ሀገር መገበያያ ገንዘብ (የአሜሪካ ዶላር፣ የእንግሊዝ ፓውንድ፣ ወይም ዩሮ) በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ (Bank Guarantee) ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ::
  • ማሳሰቢያ: የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒክ ዋና ሰነድ (Technical Original) ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መቅረብ አለበት::

3. የሰነድ አቀራረብ እና ማቅረቢያ ደንቦች

  • ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 45 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
  • ሰነዶቹ በአንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት (ዋና እና ቅጂ) እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ (ዋና እና ቅጂ) በሚል በግልፀ በሚታይ መልኩ በመጻፍ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  • ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በግልፀ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::

4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ መርሃ-ግብር

  • የጨረታ መዝጊያ: ጨረታው በ46ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ
  • የጨረታ መክፈቻ: በዕለቱ 4:30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል::
  • ማሳሰቢያ:የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::

5. የድርጅቱ መብቶች እና አድራሻ

  • ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • አድራሻ: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
  • ኢሜይል (e-mail): procurement@press.et

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Press Agency re-tenders internationally for pre- to post-press printing machines: sheet-fed offset press, folding, paper cutting, perfect binding, saddle stitching and laminating machines, a heavy-duty printer and thermal CTP. Open to local and foreign bidders.
Save Tender

Ethiopian Press Agency – Supply of Printing Machinery from Pre-Press to Post-Press (Re-Bid, ICB)

READ MORE
Oromia Pipe Factory PLC – Supply, Installation and Commissioning of HDPE and uPVC Pipe Testing Machi...

READ MORE