በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ20 ሳይቶች የቨርሚ ኮምፖስት ሼድ ግንባታ
በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ግልፅ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ግብርና ቢሮ በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች ሊያሰራ በያዛቸው የቨርሚ ኮምፖስት ሼድ ግንባታ እና ተያያዥ ስራዎችን ፣ በግንባታ ዘርፉ የተሰማሩ ተቋራጮችን በሚከተሉት መስፈርቶች በመለየት በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
ስለሆነም:-
- ደረጃቸው GC-4/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / Tin Number ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣ በስራና ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተመዘገበና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው መረጃ የሚያቀርቡና እና በጨረታ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልፅ ከገቢዎች የተሰጠ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ፤
- በክልሉና በቢሯችን ውስጥ በግንባታ ስራ ተሰማርተው ከሆነ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ያላቸውና ስራዎችን ያላስተጓጎሉ ወይም ያላቋረጡ፤
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡትን የቴክኒክና የገንዘብ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ስራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ስራ ሂደት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ ለአንድ ሳይት የማይመለስ 1000 (አንድ ሺ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነድ እንዲሁም የጨረታ ዋስትናም ለብቻው እያንዳንቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት እስከ 20ኛው ቀን ይሆናል።
- ኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መፃፍ አለበት ፣ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት። ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለ ከ20 ተከታታይ ቀን በኋላ በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ታሽጎ 4:30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000(ሁለት መቶ ሺ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የክፍያ ማዘዣ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የባንክ ዋስትና ሲሆን ይህም 45+28 (73)ቀን የሚቆይ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ከቀረቡት ሣይቶች ውስጥ የሚጫረቱበትን ሳይት ለይተው በግልፅ በመፃፍ መለየት አለባቸው::
- አንድ ተጫራች ከአንድ እስከ ሶስት ባሉ ሳይቶች ላይ መወዳደር የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሳይት በላይ ለሚጫረት ተቋራጭ ለእያንዳንዱ ሣይት የተሟላ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ከቢሮው ጋር ሌላ ፕሮጅክት ያላቸው ከሆነ እየተሰራ ያለው ግንባታ 80% እና ከዚያ በላይ የደረሰ መሆን አለበት::
- የመወዳደሪያ ሳይቶቹም የሚከተሉት ናቸው::
| ሎት | የፕሮጀክቱ መገኛ ቦታ | የጨረታ ማስከበሪያ (ብር) |
| 1 | ምስ/ጎጃም ዞን፣ ሸበል ወረዳ፣ ትኬ ቀበሌ፣ ጭማገል ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 2 | ምስ/ጎጃም ዞን፣ ደጀን ወረዳ፣ ሞገን ቀበሌ፣ ጤቅ ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 3 | ምዕ/ጎጃም ዞን፣ወንበርማ ወረዳ፣ ሸንዲ ቀበሌ ወይኒቱ ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 4 | ምዕ/ጎጃም፣ደንበጫ ወረዳ፣ ለጀት ቀበሌ ጉላ ች/ ጣቢያ | 200,000.00 |
| 5 | ሰ/ጎጃም ዞን፣ደቡብ አቸፈር ወረዳ፣ ቀልጣፋ ቀበሌ፣ ከሴቲ ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 6 | አዊ ብ/ዞን፣ ዳንግላ ወረዳ፣ ጊሣ ቀበሌ ሣሃራ ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 7 | አዊ ብ/ዞን፣ ጓንጓ ወረዳ፣ ጅባይታ ቀበሌ ጅባይታ ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 8 | ደ/ጐንደር ዞን፣እንዳቤት ወረዳ፣ ወለሽ ከተማ FTC | 200,000.00 |
| 9 | ደ/ጐንደር ዞን፣ ፎገራ ወረዳ፣ ቆሃር ቀበሌ ቆሃር ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 10 | ማዕ/ጎንደር ዞን፣ምዕ/ደንቢያ ወረዳ፣ ተዘባ ቀበሌ መልካም ውኃ | 200,000.00 |
| 11 | ማዕ/ጎንደር ዞን፣ ነባሩ ጭልጋወረዳ፣ ጫንድባ ቀበሌ ጫንድባ ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 12 | ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ፣ አዲስጌ ቀበሌ አዲስጌ ች/ጣ | 200,000.00 |
| 13 | ሰ/ሸዋ ዞን፣ኤፍራታና ግድም ወረዳ፣ ላይኛዉ አጣዬ ቀበሌ፣ ፊረደ ውኃ ች/ጣ | 200,000.00 |
| 14 | ሰ/ሸዋ ዞን፣መንዝ ማማ ወረዳ፣ ቀበሌ 02፣ አምባ ዉኃ ች/ጣ | 200,000.00 |
| 15 | ደ/ወሎ ዞን፣ ቃሉ ወረዳ፣ 032 ቀበሌ፣ FTC | 200,000.00 |
| 16 | ደ/ወሎ ዞን፣ ጃማ ወረዳ 06 ቀበሌ፣ FTC | 200,000.00 |
| 17 | ሰ/ወሎ ዞን፣ መቄት ወረዳ 017/በረከዝ ቀበሌ፣ በረከዝ ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 18 | ሰ/ወሎ ዞን፣ ሀብሩ ወረዳ/ ገራዶ/04 ቀበሌ ገራዶ ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 19 | ኦሮሞ ብ/ዞን፣ ዳዋጨፋ ወረዳ፣ ሲትር ቀበሌ፣ ሲትር ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
| 20 | ዋግ/ብ/ዞን፣ ሰቆጣ ከተማ፡ 016/ፈቅረ ሰላም/ ቀበሌ፣ ሩባሪያ ች/ጣቢያ | 200,000.00 |
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251-0582-26-2891 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ:: በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፤ ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
✨ messages.ai_summary
The Amhara Region Bureau of Agriculture seeks GC-4/BC-5 or higher contractors to build vermicompost sheds and related works at 20 sites across Gojjam, Awi, Gondar, Shewa, Wollo, Oromo and Wag zones. Bidders may bid for up to 3 sites. Open bid.
