ድርጅታችን ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፓወር ፋክተር ኮሬክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገጠም ይፈልጋል::
Yiha Real Estate P.L.C (ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)
የፓወር ፋክተር ኮሬክተር ግዢ የወጣ ግልፅ ጨረታ
ድርጅታችን ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፓወር ፋክተር ኮሬክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገጠም ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራቾች የፓወር ፋክተር ኮሬክተር ለመግጠም የጥናት አናሊሲስ በመስራት የእቃው ዋጋ እና የሙያው ዋጋ ከነ ሙሉ ዕቃው በማቅረብ ሥራውን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል አስሮ ማሰራት ስለሚፈልግ፣
በዚሁ መሰረት
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል 2ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 07 መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሠነድ በመግዛት አናሊሲስ ለመስራት በድርጅቱ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ የማሽኖቹን ጥናት ፋሲሊቲ ሰርቪስ በተገኙበት መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርፍተኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል::
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20 (ሀያ ሺ) በይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሥም ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራች ከዚህ በፊት በዚሁ ሥራ በጨረታ የተሳተፈባቸው ድርጅቶች (መ/ቤቶች) የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል::
- ተጫራች የሚያቀርበውን የጨረታ ሰነዱ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ለየብቻ ለይቶ በማሸግና በኢንቨሎፑ ላይ የተጫራች ማንነት በመግለፅ ክብ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል::
- ተጫራች ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ካላሟላ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል::
- በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦቹን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ወደ ፋይናንሻል ግምገማ ያልፋሉ::
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 7 /በሰባተኛው የሥራ ቀን/ በስራ ሰዓት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይሆናል::
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 7 /በሰባተኛው የሥራ ቀን/ በስራ ሰዓት ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይሆናል::
- ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላሉ::
አድራሻ:- አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት "ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር - 12
ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር- የቢሮ 0115580129/0115576954/ ሞባይል - 0922079575 /0911397239
ማሳሰቢያ:- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
✨ messages.ai_summary
Yiha Real Estate PLC seeks contractors to study, supply and install a power factor corrector with all materials and labour. Bidders need a renewed trade licence, TIN, VAT registration, a professional competency certificate and good performance records from similar work.
