ኩባንያችን ድሬዳዋ የሚገኘውና የኩባንያው ንብረት የሆነውን ባለ 4 ፎቅ ህንፃ ላይ ለተለያዩ ተከራዮች ተከራይቶ የሚገኝ ለኮሜርሻል አገልግሎት የሚውለውን 4ፎቅ የሆነ የህንፃውን ክፍል ለማስጠበቅና ለማፀዳት እንዲሁም አዲስ አበባ ለሚገኙ የተለያዩ የኩባንያው ቅርንጫፎች ቢሮን ለማፀዳት በዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማስጠበቅና ማፀዳት ይፈልጋል::
Nib Insurance Company S.C (ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)
የጥበቃ እና ፅዳት አገልግሎት ግዥ
ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :-PPFMS-008/2026-27
ኩባንያችን ድሬዳዋ የሚገኘውና የኩባንያው ንብረት የሆነውን ባለ 4 ፎቅ ህንፃ ላይ ለተለያዩ ተከራዮች ተከራይቶ የሚገኝ ለኮሜርሻል አገልግሎት የሚውለውን 4ፎቅ የሆነ የህንፃውን ክፍል ለማስጠበቅና ለማፀዳት እንዲሁም አዲስ አበባ ለሚገኙ የተለያዩ የኩባንያው ቅርንጫፎች ቢሮን ለማፀዳት በዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማስጠበቅና ማፀዳት ይፈልጋል::
ስለሆነም በተጠቀሰው ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያለው እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ድርጅት መወዳደር ይችላል::
1. ተጫራቾች:-
1.1 ለ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
1.2 የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
1.3 ለሚሰጠው አገልግሎት የመድህን ዋስትና ማቅረብ የሚችል
1.4 የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
1.5 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው
1.6 የፌደራል ፖሊስ የግል ጥበቃ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
1.7 ተጫራቾች ስራና ሠራተኛን የማገናኘት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ከዚራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የኩባንያው ንብረት የሆነ ህንፃ መመልከት ይችላሉ::
3. ተጫራቾች የአገልግሎት ዋጋቸውን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው መልኩ ማቅረብ አለባቸው::
| ተ.ቁ | የመስሪያ ቦታ | የሰራተኛው አይነት | ብዛት | የወር ደመወዝ ተ.እ.ታ ጨምሮ |
| 1 | ድሬዳዋ | ወንድ ጥበቃ | 15 | |
| ሴት ፈታሽ | 1 | |||
| የፅዳት ሰራተኛ | 7 | |||
| 2 | አዲስ አበባ | የፅዳት ሰራተኛ | 18 |
4. ተጫራቾች ዋጋቸውን ለድሬዳዋ ህንፃ የጥበቃ እና የፅዳት ለአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮዎች የፅዳት አገልግሎት በማለት በተናጠል ማቅረብ ይችላሉ:: ነገር ግን ለድሬዳዋ ህንፃ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጥበቃ እና ፅዳት አገልግሎት ዋጋቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
5. ተጫራቾች የሚሰጡት የአገልግሎት ዋጋ ለአንድ ጥበቃ ሰራተኛ እና ለአንድ ፅዳት ሰራተኛ ተብሎ መገለፅ ይኖርበታል::
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ ደምበል ሲቲ ሴንተር 11ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1101 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
7. ጨረታው ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ግዥ ንብረትና ፋሲሊቲ አስተዳደር አገልግሎት ቢሮ (ቢሮ ቁጥር 1101) ውስጥ ይከፈታል::
8. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት መፈረም እና ስራውን መጀመር አለበት::
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው::
10. ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
11. ድሬዳዋ ለሚገኘው ህንፃ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት የሚሰጡ ተጫራቾች ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ህጋዊ ቢሮ ሊኖራቸው ይገባል::
12. ቦታውን በአካል ተገኝቶ መመልከት ለሚፈልጉ ተጫራች ከታች ለተጠቀሱት የኩባንያው ሰራተኛ በመደወል ቦታው የሚገኝበትን አካባቢ መረዳት ይችላሉ::
- ድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ከዚራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የኩባንያው ህንፃን ለመመልከት ለአቶ ዋሲሁን አበራ በስልክ ቁጥር 0911-02-03-34
- አድራሻ:-ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)
ደምበል ሲቲ ሴንተር 11ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1101 (ሊፍት ቁጥር 2 ወይም 3 በመጠቀም)
ስልክ:- 011-5-54-49- /011-5-54-01-76 (አዲስ አበባ)
