የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቤተሰብ ህክምና ደብተር (Family Health Insurance Book) ህትመት ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር RE-DBE/NCB/PR/001/2026/27 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቤተሰብ ህክምና ደብተር (Family Health Insurance Book) ህትመት ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር RE-DBE/NCB/PR/001/2026/27 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
1. ተጫራቾች ከጨረታው መልስ ጋር የሚከተሉትን ተጨማሪ ሰነዶችንያቀርባሉ:
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያቁጥር /T.I.N/
- የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ ተጫራቹ የግብር ግዴታ የተወጣ በመሆኑ ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ የጽሁፍ ማስረጃ (ጊዜውያላለፈበትመሆንይኖርበታል)
- የተ.እ.ታክስ /VAT/ ሰርተፊኬት
- የመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደር የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበት ፎርማት ተሞልቶ የተጫራቹ ድርጅት ፊርማና ማህተም የተደረገበት
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 15,000 በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው
3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር/ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ታወር ሁለት በባንኩ እግረኛ መግቢያ ክፍያውን ፈጽመው ባንኩ በተከራየው ህንጻ ላይ (ኪሜድ ህንጻ ላይ) 1ኛ ፎቅ ከግዥ ቡድን ቢሮ ሶፍት ኮፒውን መውሰድ ይችላሉ::
4. የጨረታ ሰነድ ለተጫራቾች መሸጥ የሚጀምረው ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ነው::
5. ተጫራቾች ጥያቄ ካላቸው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል::
6. ተጫራቾች ከጨረታ መክፈቻ ሰአት በፊት ናሙና እና ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባንኩ በተከራየው ህንጻ ላይ (ኪሜድ ህንጻ ላይ) ግዥ ክፍል ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ::
8. ጨረታው ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ላይ ታሽጎ ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:05 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
9. ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
10. ለበለጠ መረጃ 0115-57-80-88 መደወል ይቻላል::
