ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ለፋብሪካ ግብዓት የሚውል 6,700 ኩ/ል የተዳመጠ ጥጥ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Bahir Dar Textile Share Company (የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፣ ባ/ጨ/ጨ/ግ/አቅ/001/2019
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ለፋብሪካ ግብዓት የሚውል 6,700 ኩ/ል የተዳመጠ ጥጥ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡
- ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-
- ሕጋዊ ፈቃድ:- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT):- በቫት (VAT) ተመዝጋቢ ሆነው የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና መጠን የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ አቀራረብ እና አሰጣጥ:-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አ/ማ ወይም አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሃሳብ የያዘው ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናው እና ኮፒው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ሁኔታ:-
- የጨረታው መክፈቻ ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ጨረታው በ21 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30 ባህርዳር ጨርቃ ጨርቅ አ.ማ ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ዕለት ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መብት:-
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ
ስልክ ቁጥር:
- ባህር ዳር 0582200080/0900911834
- አዲስ አበባ 0115531381/0115539742
* ቦታ አድራሻ፣ ባህር ዳር ከተማ ግሽ አባይ ክ/ከተማ ቀበሌ 10
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር
✨ messages.ai_summary
Bahir Dar Textile Share Company seeks bidders to supply 6,700 quintals of ginned cotton as factory input via open tender. Bidders must hold a renewed trade license, pay current taxes, have a TIN, be VAT-registered with certificate, and submit a bid security of 1% of total price via CPO or bank guarantee.
