የደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ኪራይና መለዋወጫዎች፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች እና ሃንድ ኮምፓክተር በግልጽ ጨረታ ለመግዛትና ለማከራየት ተጫራቾችን ይጋብዛል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን አገልግሎት
የአገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል
- የጽዳት እቃዎች (በሎት)
- የደንብ ልብስ (በሎት)
- ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች (በነጠላ)
- የተሽከርካሪና ማሽነሪዎች ኪራይ (በነጠላ)
- የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ (በነጠላ)
- የኮንስትራክሽን ማተሪያሎች (በነጠላ)
- ሃንድ ኮምፓክተር (በነጠላ)
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- አግባብ ባለው የመንግስት ተቋም የተሰጠ የምዝገባ የምስክር ወረቀት
- አግባብ ባለው የመንግስት ተቋም የተሰጠ ወይም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 500,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገበ መሆንን፡፡
- ተወዳዳሪዎች በግብር አመቱ ተገቢውን የታክስና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችና አገልግሎቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሰጡትን ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% ከነቫቱ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት አለባቸው፡ ፡ከእነዚህ ውጭ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ /የጨረታ ሰነዱ/ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ45 ቀን /አርባ አምስት ቀን/ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ማግኘት ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን ከግዥና ፋ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እስከ ቀኑ 11:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ፖስታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ የሌለው ወይም የጨረታ ማስከበሪያው የሚያንስ ከሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞላው ዋጋ የማይነበብና ተጫራቹም ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች መሙላት የሚችሉት መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ሰነድ ብቻ ሲሆን በሌላ ወይም በራሱ የዋጋ መሙያ ሞልቶ ቢያቀርብ ተጫራቹን ከውድድር ውጭ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
- በጨረታ በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡በተጨማሪም በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን በ11ኛው ቀን ከጧቱ 3:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ/አገልግሎት ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን መ/ቤት እንደአስፈላጊነቱም በደሴ ከተማ የአስተዳደር ክልል ውስጥ እንዲያቀርብ ሲጠየቅ በራሱ ማጓጓዣ፣ማስጫኛ እና ማውረጃ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው ለጽዳት እቃና ለደንብ ልብስ በሎት ሲሆን ከእነዚህ ውጭ ያሉትን በነጠላ ዋጋ ውድድር ይሆናል፡፡
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 312 91 72/ 033 311 10 41/1048/ 10 59 በመደወል ማግኘት ይቻላሉ፡፡
አድራሻ ፡- ካራጉተ መስጅድ ፊት ለፊት
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት
✨ messages.ai_summary
Dessie City Roads Authority invites bids for cleaning supplies and uniforms (by lot), electronics, vehicle/machinery rental, spare parts, construction materials, and a hand compactor (individually). Bidders must submit registration certificate, business license, TIN, VAT registration if purchase exceeds ETB 500,000, and tax clearance.
