Tender Detail

Tender Details

  • Company የጅማ ዩኒቨርሲቲ
  • Address , Phone: 0471123895
  • Website
  • Deadline06 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 50,000.00 (CPO ወይም Bid bond)
  • opening dateጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:15 ሠዓት
  • Categories Pharmaceutical Products

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ አገልግሎት የሚውሉ መድሐኒቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ አገልግሎት የሚውሉ መድሐኒቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት-1 የመድሐኒት ግዥ

በዚሁ መሠረት በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የተለያዩ የመድሐኒቶች አቅርቦት ጋር አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና ወቅታዊ የግብር ግዴታዎችን እየተወጡ ያሉና በጨረታ ተካፋይ ለመሆን እንዲችሉ የሚገልጽ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ዋስትና (Bid bond) እንዲሁም በማይክሮ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸዉ ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የጨረታ ዋስትና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለአሸነፉባቸው የተለያዩ የመድሐኒቶች አቅርቦቱን የሚፈጽሙት በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማቅረብ ነው፡፡
  4. ተጫራቾች ማናቸውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታዎችን በሚያቀርቡት ያንዳንዱ የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ቢሮ ወይም የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት (ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ከብስራት ሆቴል 100 ኪ.ሜ ከፍ) ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሠዓት በግንባር መረጃዎችን ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

የጨረታው ሠነድ የሚዘጋውና የሚከፈተው

የጨረታ ሠነድ የመድሐኒት ግዥ እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው በጅማ ከተማ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈተዉ በዛዉ ዕለት ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:15 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ቢሮ የሚከፈት ይሆናል ።

  • የበለጠ መረጃ ቢያስፈልግዎት በስልክ ቁጥር 0471-116912 ወይም 0111550621 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • ዩኒቨርስቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ፋርማሲ

✨ messages.ai_summary
Jima University seeks to purchase medicines for its Model Community Pharmacy via open tender (Lot 1). Bidders must be legal suppliers with a valid trade license, MoF supplier registration, VAT registration, tax compliance, and a support letter from the local revenue office. Delivery is to the pharmacy store at the bidder's own transport cost.
Save Tender