ልዩ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ/ማ ብቁና ህጋዊ ከሆኑ የኢትዮጵያ አቅራቢዎች የDEYE Brand 30KW Hybrid Inverter እና 30KWh Lihium-ion Battery Storage System ግዢ፣ አቅርቦትና ዝርጋታ ሥራ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
Liyu Microfinance Institution S.C. (ልዩ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ)
የኢንቨርተርና የባትሪ ስቶሬጅ ሲስተም ግዢና ዝርጋታ የጨረታ ማስታወቂያ
ልዩ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ/ማ ብቁና ህጋዊ ከሆኑ የኢትዮጵያ አቅራቢዎች የDEYE Brand 30KW Hybrid Inverter እና 30KWh Lihium-ion Battery Storage System ግዢ፣ አቅርቦትና ዝርጋታ ሥራ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸውና በጨረታው ሰነድ የተጠቀሱትን ዝርዝር መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያዎች በመከተል እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከልዩ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ/ማ ዋና መ/ቤት፣ ሰው ሀይልና ንብረት አስተዳደር ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት አየር ላይ በማዋል ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ፣ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ ሞልተው፣ የቴክኒካል ፕሮፖዛልና የፋይናንሻል ፕሮፖዛልን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች በማድረግና በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ብቻ ማስገባት አለባቸው።
3. የጨረታ መክፈቻ
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀን በኋላ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በልዩ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ/ማ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ መወዳደሪያ ያስገባውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናነት በባንክ የተረጋገጠ (C.P.O.) ከቴክኒካል ፕሮፖዛሉ ጋር ማቅረብ አለበት። ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
5. የማስገቢያ አድራሻ
የጨረታ ሰነዱን ለማስገባት:-
ልዩ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ/ማ
ሰው ኃይልና ንብረት አስተዳደር
ከ22 ጎላጎል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ከKB Mall በስተቀኝ በኩል ገባ ብሎ።
ለበለጠ መረጃ:-
ስልክ ቁጥር:- 011 557 8442
