የባለአክሲዮኖች 27ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ - ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
Vision Fund Micro Finance Institution S.C (ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ)
የባለአክሲዮኖች 27ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤ ጥሪ ማስታወቂያ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1) እና 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 2 እና 13 መሰረት የቪዥንፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 27ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሕዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 08፣ የቤት ቁጥር 681 በሚገኘው ሀይሌ ግራንድ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1. ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1 የማኅበሩ ስም፡- ቪዥንፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማህበር
1.2 የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 06፣ የቤት ቁጥር 917 https://www.visionfundmfi.com
1.3 የአክሲዮን ማህበሩ ምዝገባ ቁጥር፡- BL/AA/2/0009865/2007
1.4 የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- ብር 5,282,077,000.00
1.5 የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- ብር 5,282,077,000.00
2. የጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.1 የባለአክሲዮኖች 27ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.1.1 የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
2.1.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጥቆማ ማካሄድና መምረጥ፣
2.1.3 እ.ኤ.አ. የ2025/26 የሂሳብ ዘመን የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና በቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፣
2.1.4 እ.ኤ.አ. የ2025/26 የሂሳብ ዘመን የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ፣ መወያየትና በቀረበው ሪፖርት ላይ ውሳኔ ማሳለፍ፣
2.1.5 እ.ኤ.አ. የ2026/27 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን መሰየምና ክፍያቸውን መወሰን፣
2.1.6 ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማን መቀበልና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን፣
2.1.7 እ.ኤ.አ. በ2025/26 በጀት ዓመት በተገኘ የተጣራ ትርፍ አደላደል ላይ በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
2.1.8 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የ2026/27 ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያና ወርሃዊ አበል መወሰን፣
2.1.9 የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፣
2.2 የባለአክሲዮኖች 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.2.1 የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
2.2.2 የተቋሙን ካፒታል ለማሳደግ በቦርዱ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፣
2.2.3 የተቋሙን መመስረቻ ጽሁፍ ለማሻሻል በቦርዱ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፣
2.2.4 የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፣
3. ማሳሰቢያ
3.1 በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸው ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባኤው ከመካሄዱ ከሶስት ቀን በፊት በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት (አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 06፣ የቤት ቁጥር 917) በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካዩ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ በጉባኤው ተሳትፎ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ስለመሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
3.2 የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
