የወተት ላሞች፣ መኖ፣ ዶሮ፣ የንብ መንጋና ቀፎ፣ የወተት ዕቃዎች፣ የመኖ ዘር፣ የእንስሳት መድኃኒትና የመኪና ጎማ ግዥ - የአፋር ክልል የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ሠመራ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ 2019 በጀት ዓመት ለማከናወን ከቀዳቸው ግዥዎች ውስጥ የተሻሻሉ የወተት ላሞች፣ የተመጣጠነ መኖ ፣የተሻሻሉ የዕንቁላል ጣይ ዶሮ፣ የንብ መንጋ የንብ ቀፎ እና የንብ ማነቢያ ቁሳቁሶች፣ የወተት ማለቢያ ዕቃዎች፣ የእንስሳት መኖ ዘር፣ የእንስሳት መድኃኒት እና መገልገያ ዕቃዎች እና የመኪና ጎማ ግዥ በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፡-
- 1.1 በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- 1.2. የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
- 1.3.የግብር ከፍያ መለያ ቁጥር/TN No/ ያለው
- 1.4.ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለበት እና
- 1.5 የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ከአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሮክቶሬት ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የሕጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/Bid Bond /ለውድድር የሚያቀርቡት ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና ለተጠየቀው ወይም ናሙና የሚያስፈልጉ ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡት የውድድር ጥያቄ መ/ቤቱ አይቀበልም፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው የሥራ ቀን 4:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በዕለቱ 4:30 ሰአት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ ግዥና ፋይ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በቢሮ ግዥናፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ከፍል በቢሮ በአካል በመገኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ
ሠመራ
✨ messages.ai_summary
Afar Region Livestock and Fisheries Development Bureau seeks local open-tender suppliers for improved dairy cows, balanced feed, improved layer chickens, bee colonies, hives and beekeeping materials, dairy utensils, animal feed seed, veterinary drugs and supplies, and vehicle tires. Bidders must hold a valid trade license, tax ID, and submit a CPO.
