በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ቤተ ክህነት ሰሚት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ግልጽ የብረት በርና መስኮት ጨረታ
Semit M/T/St Giorgis & St
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ቤተ ክህነት
ሰሚት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ግልጽ የብረት በርና መስኮት ጨረታ
የደብሩ ሰበካ ጉባዔና ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ለሚያስገነበው አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የብረት መስኮትና በር (Metal Window & Door) ሥራ ለማሠራት በአማራጭ፡
Lot-1 የብረት መስኮት ሥራ
Lot-2 የብረት በር ሥራ ለማሰራት የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ፡፡ ለመጫረት መሟላት የሚገባቸው መሥፈርቶች
- የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፡፡
- አግባብ ያለው የሥራ ልምድና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100 ሽህ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለ90 ቀን ፀንቶ የሚቆይ የባንክ ጋራንቲ(ዋስትና) ለሰሚት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ማስያዝ የሚችል፡፡
- ለሥራው የሚያስፈልገውን ማሽነሪና የሰው ኃይል ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካልና የፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ በተላያዩ ኢንቨሎፕ(ማሸግያ) በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የእጅ ዋጋ ወይም ማቴሪያል አቅርቦት ጨምሮ ከሁለቱም የተሻለውን መምረጥ የቤተክርስቲያኗ ኃላፊነት ይሆናል፡፡
- በተክርስቲያኗ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቷ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ መክፈቻ በ15ኛ ቀን ሆኖ፣ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ ቀጣይ በሥራ ቀን የሚከፈት ሆኖ የጨረታ ሰነዱም እስከ ጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ገብቶ ተጫራቾች፣ ኮሚቴውና የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት በተገኙበት በዛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ዋጋ ሞልተው ከመመለሳቸው በፊት የሳይት መልከታ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ደብሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0911157061/0913001541
የደብሩ ህንጻ አሠሪ ኮሚቴ
