የአብክመ ጤና ቢሮ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ግዥ ለመፈፀም የወጣ ግልፅ ጨረታ
አብክመ ጤና ቢሮ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ጤና ቢሮ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ግዥ ለመፈፀም የወጣ ግልፅ ጨረታ
- ግዥ የሚፈፀመው በቅርቡ ተሻሽሎ በወጣው የመንግሥት የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 306/2018 እና የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 144/2018 መነሻ በማድረግ ነው።
1. የተወዳዳሪዎች ቅድመ ብቃት መስፈርቶች
- ተጫራቾች በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 144/2018 አንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 1 ከ"ሀ" እስከ "ሸ" የተዘረዘሩትን የተወዳዳሪዎች ቅድመ ብቃት መስፈርቶችን ማለትም የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፣የታክስ ክሊራንስ፣ የሙያ ምስክር ወረቀት እና ሌሎች መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊ ናቸው የሚላቸው ደጋፊ ሰነዶች ማቅረብ አለባቸው፣
- የሚገዛው የህክምና መሳሪያ ጠቅላላ ዋጋ ከ500000.00/አምስት መቶ ሽህ ብር በላይ ስለሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው በአማራ ክልል ጤና ቢሮ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 በሚገኘው ዋና መ/ቤት ውስጥ በግዥ ፋይናንስ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት ሲሆን ሰነዱን ለመግዛት ብር 1500/አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር መክፈል ያስፈልጋል፤
- አንድ ተጫራች ከአንድ በላይ የሆነ የመጫረቻ ሰነድ መግዛትም ሆነ ሞልቶ በማቅረብ የሚሳተፍ ከሆነ ከጨረታው ውድቅ እንዲሆን ይደረጋል ።
2. የቴክኒክ ፍላጎት መግለጫ ስለማዘጋጀት
- ተጫራች የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ለየብቻው በማዘጋጀትና በተናጠል በማሸግ መቅረብ አለበት፡፡የሚዘጋጀው የቴክኒክ ፍላጎት መግለጫ የውሉ አንድ ክፍል በመሆን የአቅርቦቱን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ጥቅም ላይ ይውላል፤
- ጨረታውን ለመገምገም በሥራ ላይ የሚውሉትን ዘዴዎች፣ለዚሁ ግምገማ የሚያገለግሉትን መስፈርቶች እና እንደአስፈላጊነቱ ለመስፈርቱ የሚኖረውን የነጥብ ድርሻ ከተጫራች መመሪያው ጋር ተያይዞ ቀርቧል።
3. የጨረታ ቅፅና የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ
1/ ተጫራቾች በመደበኛ የጨረታ ሰነድ የቀረቡትንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅፆችን ሞልተው መመለስ ይጠበቅባቸዋል ።
2/ የሚዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዋጋን፣ ታክስን እና ሌሎችን ከዋጋ አቀራረብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በግልፅ ለማመልከት የሚያስችል እንዲሁም የጨረታ ግምገማን ግልጽና ቀልጣፋ ማድረግ የሚችል መሆን አለበት።
3/ የሚዘጋጀው የጨረታ ቅፅ በተቻለ መጠን ዕጩ ተወዳዳሪው ግልፅ የሆነ የመወዳደሪያ ሐሳብ እንዲያቀርብ የሚያስችል፣ የጨረታ አከፋፈቱን መረጃ የሚያረጋግጥ፣ ጨረታውን የሚያደናቅፉ ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ የሚከላከል እና ተጫራቹ ላቀረበው የመወዳደሪያ ሐሳብ ሙሉ ኃላፊነት እንዲወስድ የሚያደርግ ስለሆነ በሚመለከታቸው ቦታዎች ሞልተው ፊርማውና የድርጅቱን ማህተም አድርገው መመለስ ያስፈልጋል።
- በመደበኛ የጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚገለጹ እና በተጨማሪነት የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች እና ቅፆች ዓይነት እና ብዛት በተመለከተ ከተጫራች መመሪያው ጋር ተያይዞ የቀረበ ስለሆነ ቅጾችን ሞልቶ ማቅረብ ያስፈልጋል፤ሙስና ላለመፈጸም ቃል የሚገባበትን ቅጽና ሌሎች በተጫራቾች የሚሞሉ ቅፆች መኖራቸውንና ተሞልተው እንዲቀርቡ ማሳሰቢያ መቀመጡን ማረጋገጥ ።
4. ስለ ናሙና አቀራረብ
- የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ተጫራቾች በጨረታው ካሸነፉ በኋላ ውል ከመያዛቸው በፊት/ውል ከያዙ በኋላ ካሸነፉት የህክምና መሳሪያ ውስጥ እንደአስፈላጊነቱ ለቢሮው በናሙና እንዲቀርብ ከጠየቀ የሚፈለገውን ናሙና ጤና ቢሮ ድረስ በተጠየቀ በአምስት ቀን ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።በተጫራቾች የሚቀርበው ናሙና በቴክኒክ ገምጋሚና ፈታሽ ኮሚቴ ከታመነበት ውሉ ሊያዝና ሌሎች አቅርቦቶች እንዲቀጥሉ ትዕዛዝ ይሰጣል ፤
- የቀረበውን ናሙና ምርመራ ከተደረገ በኋላ ለተጫራቾች ተመላሽ ይደረጋል። ተጫራቾች ያቀረቡትን ናሙና የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ካልወሰዱ በውርስ ለመንግሥት ገቢ እንደሚደረግ መግለጡን።
5. በጨረታ ሰነድ ላይ ስለሚደረግ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ
ተጫራቾች በአዋጁ አንቀፅ 43 መሠረት በአብክመ ጤና ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ላይ የማብራሪያ ወይም የማሻሻያ ጥያቄያቸው ካላቸው ሊያቀርቡ ይችላሉ። በዚህ መመሪያ አባሪ 11 ላይ በተገለፀው መሰረት ጨረታው ለዕጩ ተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ዝቅተኛ ጊዜ 20 ቀናት ስለሆነ በጨረታ ሰነድ ላይ ስለሚደረግ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ መጠየቅ የሚቻለው ጨረታው ሊዘጋ 10 ቀናት እስኪቀረው ድረስ ባሉ ቀናት ብቻ ነው ፤ከ10ኛው ቀን በኋላ ለቀረበ ማብራሪያ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ መሥሪያ ቤቱ ምላሽ ለመስጠት አይገደድም።
6. የጨረታ ቋንቋ
የሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ እና በመደበኛ የጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚገለጹ እና በተጨማሪነት የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች እና ቅፆች የሚዘጋጁት በአማርኛ ቋንቋ ሲሆን ቴክኒካል ሰነዱ ለቴክኒክ ግምገማ እንዲያመች እንደ አስፈላጊነቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ መቅረብ ይችላል።
7. የመጫረቻ ዋጋ
ተጫራቾች የሚሰጡት የመጫረቻ ዋጋ በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ያልተመሰረተ፣ በጨረታው እና በውል አፈፃፀም ወቅት የማይለዋወጥ ፅኑ ዋጋ መሆን አለበት ።
8. የመጫረቻ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ
የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ ለ45 (አርባ አምስት) ቀናት ይሆናል።ሆኖም ጤና ቢሮው ጨረታው ውስብስብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የግምገማ ሂደቱ ከ45 (አርባ አምስት) ቀናት በላይ ከወሰደ የመጫረቻ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ ለተጨማሪ ቀናት እንዲያራዝሙለት ተጫራቾችን ይጠይቃል።የመጫረቻ ሰነድ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ማራዘም በሚቻልበትና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በግዥ መመሪያ አንቀጽ 115 እና አንቀጽ 116 የተጠቀሰው ተግባራዊ ይሆናል።
9. የጨረታ ማስከበሪያ
ሁሉም ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጠቅላላ ግዥውን ዋጋ መሰረት በማድረግ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ሆኖም የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) የሚበልጥ ከሆነ የ2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይችላሉ። የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አይነት እንደተጫራቹ ምርጫ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ሊሆን ይችላል።ተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን 45ኛው ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት።
10. የመጫረቻ ሰነድ አቀራረብ
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት /በሚዲያ ጥሪው ከተደረገበት ዕለት ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ ።ለማቅረቢያ ከተወሰነው ጊዜ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም። በግዥ መመሪያ አንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 7 መሰረት ካልሆነ በስተቀር ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ፣ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ ለየብቻ ተለይቶና ታሽጎ መቅረብ አለበት። የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎች የቅድመ ብቃት መገምገሚያ ሰነዶች የሚቀርቡት ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር መሆን አለበት።
11. የጨረታ አከፋፈት
ጨረታው የሚከፈተው በጨረታው ጥሪ ማለትም የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት/በሚዲያ ጥሪው ከተደረገበት ዕለት ጀምሮ በ21ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ይሆናል።ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል። ጨረታው ሲከፈትም፡-ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በቀጥታ የጨረታውን ሥነ ስርዓት ሊከታተሉ ይችላሉ።ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ በቀጥታ መከታተል ባይችል የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፤የጨረታው አከፋፈት ሂደት ላይ መሳተፍ የሚፈልግ የውስጥ ኦዲት ባለሙያ፣የፀረ- ሙስና መኮንን እንዲሁም ማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን ድርጅት ወኪል ወይም ሌሎች ፍላጎት እና ይመለከተናል የሚሉ ሰዎች በታዛቢነት መሳተፍ ቢፈልጉ የጨረታውን የአከፋፈት ሥርዓት በአካል መከታተል እንዲችሉ ይፈቀዳል፤ማንኛውም በጨረታ መክፈቻ ሥርዓት ላይ ያልተከፈተና ለተጫራቾች ያልተነበበ የመጫረቻ ሰነድ ለቀጣይ ውድድር አያገለግልም።
12. የተወዳዳሪዎች ቅድመ ብቃት ግምገማ እና ማወዳደር
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጨረታውን የተሟላ ነው ብሎ ለቀጣዩ ዝርዝር የግምገማ ሂደት ሊያሳልፈው የሚችለው በተጫራቹ የቀረበው የመጫረቻ ሰነድ በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ወቅት የተከፈተ እና በአዋጁ አንቀጽ 16 እንዲሁም በዚህ መመሪያ እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የቅድመ ብቃት መስፈርቶች ተፈላጊ ነጥቦች የሚያሟላ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው።የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የማያሟሉ ተጫራቾች፡ ወደ ዝርዝር ግምገማ አያልፍም
ሀ) የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ፤
ለ) በመሥሪያ ቤቱ የተጠየቁትን የሕጋዊነት ሠነዶች ያላቀረቡ ከሆነ፤
ሐ) በመደበኛ የጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡትን ቅጾች ሞልቶ ካልመለሰና ሌሎች ወደ ዝርዝር ግምገማ ለማለፍ የተቀመጡ ሁኔታዎችን ያላሟላ፤
13. የሒሳብ ስህተቶችን ስለማረም
የአብክመ ጤና ቢሮ በጨረታ ግምገማ ወቅት የተገኙ የሒሳብ ስህተቶችን ማረም ይችላል።አጠቃላይ የሒሳብ ስህተቶችን የማረም ተግባሩ የሚከናወነው በግዥ መመሪያ አንቀጽ 122 መሰረት ይሆናል።
14. የተሰበረ ወይም የተጋነነ የጨረታ ዋጋ
ለዕቃ ግዥ የቀረበው ዋጋ በአንጻራዊነት ሲታይ ከገበያ ጥናት ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የበለጠ ሲሆን እንደተጋነነ የጨረታ ዋጋ እንዲሁም የቀረበው ዋጋ ከ30% (ሰላሳ በመቶ) ያነሰ ሲሆን እንደተሰበረ የጨረታ ዋጋ ይቆጠራል።አጠቃላይ ግምገማውና የማረጋገጥ ስራው በግዥ መመሪያ አንቀጽ 123 መሰረት ይከናወናል።
15. ተጨማሪ ትዕዛዝ መስጠትን በተመለከተ
የአብክመ ጤና ቢሮ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፤
በማንኛውም ግዥ ለዕቃ ከብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) በላይ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000.00 (አስር ሺህ) በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች ለአቅራቢው ከሚፈፀምለት ክፍያ ላይ 3% (ሶስት) በመቶ የቅድሚያ ግብር ተቀንሶ ይቀራል ።
16. ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ስለመሰረዝ
በአዋጁ የተገለጸው ቅድመ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ የግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ማንኛውንም ጨረታ የመቀበል ወይም ያለመቀበል መብት አለው።እንዲሁም ውል ከመፈረሙ በፊት ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝና ውድቅ የማድረግ መብት አለው።
