የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግ/እ/ፕ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የእንስሳት መድሃኒት ግዥ ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡
በሸኮ ዞን የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግ/እ/ፕ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የእንስሳት መድሃኒት ግዥ ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች እና ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀርባል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል /የምትችል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የታደሰ ህጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው፡፡ በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሶስት መቶ (300) በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10/አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15(አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከሰዓቱ 9:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ኮ/ል/ጽ/ቤት
ደ/ወርቅ ስልክ ቁጥር፡- 0910997747/0929241731 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግ/እ/ፕ/ሀ/ል/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
South Bench Woreda Finance Office seeks suppliers to bid for the purchase of veterinary medicines for the Woreda Agriculture Office. Bidders must hold a valid renewed business license, supplier certificate, tax clearance, TIN, VAT registration, renewed competency certificate, and legal personality certificate. Prices must be stated in figures and words.
