Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ባህር ዳር
  • Address ባህር ዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0582221100
  • Website
  • Deadline24 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityየዘይትና ቅባቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፣ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊየን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊየን ብር/ብቻ ማስያዝ ይችላሉ
  • opening dateበ14-02-/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪና የማሽነሪ ናፍታ፣ ዘይትና ቅባት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በሎት /በጥቅል/ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ባህር ዳር


በድጋሚ የወጣ ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-06/2019

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪና የማሽነሪ ናፍታ፣ ዘይትና ቅባት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በሎት /በጥቅል/ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል፤

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው፣
  3. ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ ናፍታ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ 04/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 14/-02-/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት/ ቀን ከ04/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 14/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  9. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዘይትና ቅባቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፣ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊየን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊየን ብር/ብቻ ማስያዝ ይችላሉ፤
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በ14-02-/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፤
  11. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
    በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-322-5155 /058-222-1107 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ባህርዳር
ፖ.ሣ.ቁ.382

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

✨ messages.ai_summary
The Amhara Rural Roads Construction Agency seeks to buy fuel, diesel, oil, and lubricants for its road construction and maintenance vehicles and machinery through open lot-based bidding. Bidders must have a valid trade license, TIN, tax payment proof, and VAT registration certificate if purchase exceeds 500,000 birr.
Save Tender