Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-2-12-78-75
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 100,000.00 (CPO / Bank Guarantee / በባንክ የተረጋገጠ ቼክ)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Computer Laptop And Accessories , Office Machines And Computers , Electronics Materials

የሲዳማ ብሔ/ክል/መንግስት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ የኮምፒውተርና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን Desk top Computer ፣ Lap top Computer ፣ Photo Copier እና Printer ለመግዛት ህጋዊ አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን


ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔ/ክል/መንግስት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ የኮምፒውተርና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን Desk top Computer ፣ Lap top Computer ፣ Photo Copier እና Printer ለመግዛት ህጋዊ አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ህጋዊ መስፈርቶች፡-

  • በዘርፉ (በኤሌክትሮኒክስ ወይም በአይቲ ዕቃዎች አቅርቦት) በ2019 በጀት ዓመት የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN certificate /ከኢትዮጵያ ታክስና ጉምሩክ ባለስልጣን የተሰጠ ማቅረብ የሚችሉ
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት / VAT Registration certificate /ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • በ2019 የታክስ ክሊራንስ ሰርቲፍኬት / ወቅታዊ የመንግስት ግብር መክፈሉንና በታክስ ዕዳ አለመፈለጉን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል በመንግስት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ከፌዴራል ከክልል/ግዥና ንብረት ባለስልጣን የሚሰጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የጨረታ ሰነድ አገዛዝና አቀራረብ

  • ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር / ብቻ በመክፈል የዕቃዎቹን ዝርዝር መግለጫ /Technical Specifications / የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር / 10 / ተከታታይ የስራ ቀናት በኮሚሽኑ ግዥና ንብረት አስ/ርዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የቴክኒክ /Technical Specifications/ እና የፋይናንስ /financial offer/ ሰነዶቻቸውን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 / አንድ መቶ ሺህ ብር/ የያዘ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ CPO/ ፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/Bank Guarantee /በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • የሚገዛው የዕቃ ብዛት ዓይነትና ጥራት በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተቀመጠ ስለሆነ የጨረታ ሰነዱ ይበልጥ ተቀባይነት አለው፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ የሚሆን ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀ በኋላ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡ የውል ስምምነቱን የማይገቡ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ እንዲወረስ ተደርጎ በተጨማሪም በጥፋተኝነት ዝርዝር እንዲገቡ ይደረጋል ፡፡

3. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን፡-

  • ተጫራቾች ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አንደኛው (11ኛው) ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኤንቬሎፕ ላይ የተጫራች ድርጅት ማህተም ተደርጎ፣ ተፈርሞበትና በሰም ታሽጎ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • ኮሚሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው ፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-2127-875 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን

✨ messages.ai_summary
The Sidama Regional State Prison Commission seeks legal suppliers to provide desktop computers, laptops, photocopiers, and printers for office use. Bidders must hold a valid business license in electronics or IT supply, TIN, VAT registration, tax clearance, and supplier registration certificate.
Not stated in the notice: opening date. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender