Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline10 Nov 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ፣ በንግድ ባንክ ገቢ)
  • Bid Securityብር 500,000.00 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት
  • Categories Architectural And Construction Design , Road And Bridge Construction

በድጋሚ፡ በጎንደር እና ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያዎች የDC-4 ያልተነጠፈ የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ (SSNT-T651) - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T651

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ የጠቅላላ እና የመንገድ ስራ ተቋራጭ (GC/ RC-2 and above) የሆኑ የሃገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ በጎንደር እና ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያዎች የDC-4 ያልተነጠፈ የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክትን በዲዛይን ግንባታ (Design-Build of Unpaved DC-4 Emergency Access Road Construction at Gondar and Gambella Airports Project) የውል ዓይነት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በተጠቀሰው ምድብ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T651 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው በጨረታው ለአሸናፊነት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ማክሰኞ ህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-8025
ኢ-ሜይል፡ KidistTa@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Airlines Group seeks bidders for the design-build of unpaved DC-4 emergency access roads at Gondar and Gambella airports. Open to domestic and international bidders; local bidders must hold GC/RC-2 or above contractor grade.
Save Tender