Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት
  • Address በአብከመ ሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ፣ አማራ:ኢትዮጲያ, Phone: 0332120300
  • Website
  • Deadline22 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1,3,4,5,6,8,9፡ ብር 40,000፤ ሎት 2,7፡ ብር 10,000 (ሲፒኦ፣ ጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ ጋራንቲ)
  • opening dateበዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Categories Building Materials , Stationery Materials , Vehicle Spare Parts

የጽህፈት መሳሪያ፣ የቢሮ መገልገያ፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና ጎማና መለዋወጫ፣ የጽዳት፣ የግንባታ እቃዎችና ስሚንቶ ግዥ (9 ሎቶች, 001/2019) - በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

በአብክመ በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019

በአብክመ በሰ/ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ለግ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት ፦ ሎት፡- 1 የጽህፈት መሳሪያ ፣ ሎት፡-2 ቋሚ አላቂ የቢሮ መገልገያ ሎት፡-3 የሚገጣጠም ፈርኒቸር ሎት፡-4 ኤሌክትሮኒክስ እቃ ሎት፡-5 የመኪና ጎማ ሎት፡-6 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ሎት፡-7 የጽዳት እቃዎች ሎት 8፡- የግንባታ እና የዉሃ እቃዎች ማቴሪያል ሎት 9፡- ስሚንቶ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና ምዝገባ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተወዳዳሪዉ በግብር አመቱ ተገቢዉን የታክስ እና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል እና ላለማጭበርበር እና ላለመመሳጠር የሚሰጠዉን ፎርም ሞልቶ ማቅረብ አለበት፤፤
  3. የግዥ መጠኑ ከ500000 ( አምስት መቶ ሺህ ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆነና መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ(ማስገባት) አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የተሰጣቸዉን የጨረታ ቅጽ በአግባቡ መሙላት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች በዝርዝር በተገለጸው መሰረት ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ድረስ ያሉት ሁሉም ሎቶች 10 ኛዉ ቀን 11፡30 ድረስ ግ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 001 ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት በመምጣት መግዛት ይችላሉ ፡፡
  7. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሚወዳደሩበት እቃ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሎት1- የጽህፈት መሳሪያ ሎት፡-3 የሚገጣጠም ፈርኒቸር ሎት፡-4 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 5 የመኪና ጎማ ሎት፡-6 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ሎት 8፡- የግንባታ እና የዉሃ እቃዎች ማቴሪያል ሎት 9፡- ስሚንቶ ጨረታ ብር 40000 / አርባ ሺህ ብር/ እና ፣ሎት፡-2 ቋሚ አላቂ የቢሮ መገልገያ ሎት፡-7 የጽዳት እቃዎች ብር 10000 / አስር ሺህ/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/፤ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ጋራንት በማስያዝ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ አሽጎ (አያይዞ) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ጨረታዉ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 40 አርባ ቀን የሚቆይ ይሆናል ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታዎች ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ድረስ ያሉት በ11 ኛው ቀን 4፡00 ስአት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ስአት ይከፈታል ፡ ፡ የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራች ውጤቱ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/፤ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ጋራንት በማስያዝ በፍትህ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  11. የሚገዙት እቃዎች የማስረከቢያ ቦታ ግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ባሉ ሁሉም ንብረት ክፍሎች ዉስጥ ይሆናል፡፡ ለዚህ ም የሚዎጡ ወጭወች በሙሉ በአሸናፊዉ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፤፤
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ካስፈለገ በግዳን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0332120008 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአብክመ የግዳን ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Supply of stationery, office consumables, furniture, electronics, vehicle tyres and spare parts, cleaning, construction and water materials, and cement, in 9 lots. Bidders must provide a valid trade licence, tax clearance, and a completed anti-fraud form; VAT registration is required if the purchase exceeds 500,000 birr.
Save Tender