DKT Ethiopia – Supply of One (1) Reach Truck
DKT Ethiopia
የጨረታ ማስታወቂያ
ዲኬቲ ኢትዮጵያ (ድንቅ ክስተት ለጤና) የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ማህበራዊ ግብይትን በመከተል የቤተሰብ እቅድን ለማስፋፋት፣ ኤችአይቪን ለመከላከል፣ እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ጤናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ምርቶችን በማሰራጨት በሲቪል ማህበረሰብ ባለስልጣን በምዝገባ ቁጥር 0062 ተመዝግቦ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በኤችአይቪ እና የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የራሱን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ያለ የውጭ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፤ ለድርጅቱ የመጋዝን አገልግሎት የሚውል አንድ (01) ሪች ትራክ (Reach Truck) በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሪች ትራክ ዝርዝር መግለጫ (Reach Truck Specification):
| Specification Parameter | Required Standard / Description |
| Operator Type | Seated |
| Load Capacity | >= 1,200 kg |
| Drive / Support Arm Wheel | Polyurethane |
| Ground Clearance | 70 mm or more |
| Aisle Width for Pallet (1000 x 1200 mm) | 2,800 mm |
| Gradeability (With / Without Load) | 15% / 18% |
| Drive Type | Electric |
| Drive Motor | 5 kW or more |
| Lifting Motor | 10 kW or more |
| Overall Length | 2,400 mm or less |
| Reach Distance | 540 mm or more |
| Lifting Height | ≤ 7,000 mm |
| Warranty | Supplier to specify warranty period |
| Accessories / Spare Parts | Supplier to specify availability |
የጨረታ ደንቦችና መመሪያዎች:
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የሰነድ ማቅረቢያ መንገድ፡ ተጫራቾች የቴክኒክ (Technical Specification) እና የፋይናንሻል (Financial Offer) የጨረታ ሰነዶቻቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች (In separate sealed envelopes) በማዘጋጀት ከዚህ በታች በተጠቀሰው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ በአካል (In person) ቀርበው ማስገባት አለባቸው።
- ዕቃ ማስረከቢያ ቦታ፡ ከገርጂ ወደ ጉርድ-ሾላ በሚወስደው መንገድ ከኑና መጋዘን ቀጥሎ በሚገኘው መጋቢ መንገድ ላይ ወጋገን ባንክ ገባ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት።
- ተጫራቾች እቃውን የሚያስረክቡበትን ትክክለኛ ጊዜ (Delivery Period) በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ (Quotation) ላይ በግልጽ ማመልከት አለባቸው።
- የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ጥቅምት 11፣ 2019 ከሰዓት 11:00
- የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት፡ ጥቅምት 12 ፣ 2019 ከሰዓት 8:00
- የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተባለው ቀንና ሰዓት ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
- ድርጅቱ ማንኛውንም ጨረታ በሙሉ ወይም በከፊል ያለምንም ግዴታ የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡ +251 911 317100 / +251 911 357228
✨ messages.ai_summary
DKT Ethiopia seeks bids for one electric seated reach truck (≥1,200 kg capacity, ≤7,000 mm lift) for warehouse use. Bidders must hold a valid business license, be tax-compliant and VAT-registered, and submit technical and financial offers in separate sealed envelopes.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
