Tender Detail

Tender Details

  • Company Tis Isat Water Works PLC (የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-220-48-26
  • Websitehttps://www.tisisat.com/
  • Deadline29 Oct 2026, 3:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceበድርጅቱ ዌብ ሳይት www.tisisat.com
  • Bid Securityበሎት: ከብር 50,000 እስከ 400,000 (CPO ወይም Unconditional Bank Guarantee)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ዋናው መ/ቤት
  • Categories Pumps, Motors And Compressors , Construction Materials And Raw Materials , Machinery Rental

የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች፣ የአካባቢ ግብአት፣ የደንብ ልብስ፣ መለዋወጫ፣ የቧንቧ ፊቲንግ፣ ማጓጓዝ እና ተሽከርካሪና ማሽነሪ ኪራይ (7 ሎቶች) - ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

Tis Isat Water Works PLC (የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር)


የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን ጢስ እሳትውሃ ስራዎች የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕ እና አልትራ ሶኒክ ፊቲንግ)፣ የአካባቢ ግብአት (አሸዋ፣ ጠጠርና የግንባታ ድንጋይ)፣ የደንብ ልብስ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ፣የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንግ እና አሸዋና ግራቭል ማጓጓዝ እንዲሁም ተሽከርካሪና ማሽነሪዎችን ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁየእቃው አይነትየጨረታ ማስከበሪያየማቅረቢያ ጊዜ
ሎት 1የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕ እና አልትራ ሶኒክ ፊቲንግ)200,000.00ከ45-60 ቀናት
ሎት 2የአካባቢ ግብአት (አሸዋ፣ ጠጠርና የግንባታ ድንጋይ)300,000.00የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት
ሎት 3የደንብ ልብስ50,000.00ከ30-45 ቀናት
ሎት 4የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ100,000.00ከ45-60 ቀናት
ሎት 5ተሽከርካሪና ማሽነሪዎች ኪራይየጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረትየጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት
ሎት 6አሸዋና ግራቭል ማጓጓዝ400,000.00የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት
ሎት 7የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንግ100,000.00ከ30-45 ቀናት

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል፡፡

የተጫራቾች መመሪያ፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርቲፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቱሪ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በC.P.O ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  7. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PRS-03/2017 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  8. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10 % የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማስያዝ ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት፡፡ የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
  11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ፤ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባህር ዳር ከተማ የኩባንያው ጽ/ቤትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጹ ቦታዎች መሆን አለበት፡፡

ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡- 058-220-48-26 /058-320-25-48/ በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

✨ messages.ai_summary
Tis Isat Water Works PLC seeks suppliers for electro-mechanical items (pumps, ultrasonic fittings), local inputs (sand, gravel, construction stone), uniforms, vehicle/machinery spare parts, pipe fittings, sand and gravel transport, and vehicle/machinery rental, across 7 lots. Bidders must submit renewed business license, VAT and TIN certificates, and sector permits.
Save Tender