Tender Detail

Tender Details

  • Company ሰዎች ለሰዎች ድርጅት (Menschen Fuer Menschen)
  • Address ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 471 42 91
  • Websitehttps://en.menschenfuermenschen.at/
  • Deadline18 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceየማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Bid Securityባቀረቡት ዋጋ ልክ (ቫትን ጨምሮ) 2% በሲፒኦ (CPO)
  • opening dateከቀኑ 8፡30 ሰዓት በዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ
  • Categories Medical Equipment And Supplies

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለሚያከናውናቸው የጤና ስራዎች የሚውሉ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ከሀገር ውስጥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት (Menschen Fuer Menschen)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለሚያከናውናቸው የጤና ስራዎች የሚውሉ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ከሀገር ውስጥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ማቅረብ ከሚችሉ እና ተጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ከሚችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል። ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው

  1. በዘርፉ የተሰማሩበት የ2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፤
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ማቅረብ የሚችሉ እና
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉትን እና የታክስ ክሊራንስ ባለስልጣን በጨረታ ለመሳተፍ የተጻፈ የታደሰ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አዲስ አበባ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ በመቅረብ በማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመግዛት እንዲሳተፉ ይጋበዛል። የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ የተጠቀሱትን 4 ሰነዶች ማሳየት ግዴታ ነው። የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ይሆን ዘንድ ባቀረቡት ዋጋ ልክ (የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ) 2% በሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት አዲስ አበባ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-6 ያሉትን ካላሟሉ ከጨረታ ይሰረዛሉ።
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መጠቀም አለባቸው። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ላቀረበው የዕቃው አይነት እና መግለጫ መስፈርት (Specification) መሆን አለበት።
  8. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በአንድ ፖስታ ሌሎች የተጠየቁ የንግድ ሰነዶችን (Business Document) እና የእቃውን አይነት መግለጫ መስፈርት (Specification) በሌላ ፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው። ፖስታዎቹም የዋጋ ማቅረቢያ እና የእቃውን አይነት መግለጫ መስፈርት (Technical) ሰነድ ተብለው ተጽፎባቸው ይቀርባሉ ።
  9. ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ በትክክል መሞላት አለበት። አቅርቦቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የማይመለከተው ከሆነ በሚሰጡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ አይካተትም።
  10. ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ከሞሉ በኋላ ጠቅላላ ድምሩን ወደ ጎን እና ወደ ታችም ደምረው ማስቀመጥ አለባቸው። የድምር ስህተት ቢኖር የተሰጠው ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።
  11. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መፈረም እና ድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  12. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በተቀመጠው የዕቃ ዝርዝር በተናጠል ለእያንዳንዱ እቃ አነስተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ ይሆናል።
  13. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ስርዝ ድልዝ ካለ በአቅራቢው መፈረም አለበት።
  14. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የሥራ ቀናት ይቆያል። በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ በሚገኘው አዳራሽ ይከፈታል፡ አስረኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ አልያም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ይሆናል።
  15. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ በሶስት የስራ ቀናቶች ማቅረብ ይኖርበታል፤ነገር ግን ጥራቱ በድርጅቱ ተረጋግጦ ካልተቀበለው ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፤ ይህን ባያደርግ ግን እቃውን ማቅረብ እንዳልቻለ ይቆጠራል፤ ያስያዘ የሲፒኦ ገንዘብ (ላሸነፈው ዕቃ) ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
  16. አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለበት። ይህንን ማቅረብ የማይችል ከሆነ ምንም አይነት ክፍያ መጠየቅ አይችልም፡፡ መ/ቤቱም እንዲከፍል አይገደድም።
  17. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ ወይም በድርጅቱ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል።
  18. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለ Menschen fur Menschen ስም አዘጋጅተው በፖስታ በማሸግ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  19. የጨረታው ውጤት ጨረታ ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ ወይም በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
  20. ተጫራቾች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይችሉም።
  21. በጨረታው ተሳትፎ አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ ያሸነፈውን እቃ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ ካልቻለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (ላሸነፈው ዕቃ) ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0114 71 42 91 / 0114 71 43 53 በስራ ሰዓት ደውለው ማግኘት ይችላሉ።

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Menschen fuer Menschen seeks local suppliers for medical equipment and supplies for its health work across various regions. Eligible bidders must be legally registered in the sector and meet specified documentation requirements. The lowest-priced bidder per item wins.
Save Tender