Tender Detail

Tender Details

  • Company ጉምሩክ ኮሚሽን አዋሽ ቅ/ፅቤት
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline14 Oct 2026, 9:45 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityለግልጽ ጨረታ: ከሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ (CPO); ለሐራጅ ጨረታ: በእቃ ኮድ ብር 100,000 (CPO)
  • opening dateለግልጽ ጨረታ 04/02/2019 እና በ07/02/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00ሰአት ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 04/02/2019 እና በ07/02/2019 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል
  • Categories Electronics Materials , Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts , Cloth And Shoes

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክቅ/ጽ/ቤት 04/02/2019 እና በ07/02/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽን አዋሽ ቅ/ፅቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክቅ/ጽ/ቤት 04/02/2019 እና በ07/02/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን፤ የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉትን የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ተ.ቁየጨረታ ቦታየጨረታው ዓይነትለጨረታ የቀረቡ እቃዎችየዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከየጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
1ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትግልጽ ጨረታ እና በሐራጅጫማዎች አልባሳት የመኪና መለዋወጫ የሞባይል ቀፎና _አስስሪ_ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪዎችና ረከቦት እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 04/02/2019 እና በ07/02/2019 እስከ ጠዋቱ 3:45ለግልጽ ጨረታ 04/02/2019 እና በ07/02/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00ሰአት ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 04/02/2019 እና በ07/02/2019 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል

የጨረታ መስፈቶች ፡-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clsarance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 04/02/2019 እና በ07/02/2019 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3:45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።
  5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል።
  8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Awash Customs Branch wants to sell various confiscated contraband goods via open and auction bids at Kaliti Customs Branch. Items include clothing, car spare parts, mobile cases, electronics, food, sports goods, watches, cosmetics, eyeglasses, jewelry, soap factory machinery, and more. Bidders need a renewed trade license, VAT registration, tax clearance, and recent VAT certificate.
Save Tender