በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2019 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ባለ 2 ሜትር የ48" የኮንክሪት ቱቦዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢመአ/ሻሽ/013/2019
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2019 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ባለ 2 ሜትር የ48" የኮንክሪት ቱቦዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50,000.00(ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡ ፡ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ/በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ/አ/ን/አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይቻላል፡፡
- በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462-114-616 መጠቀም ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Roads Administration's Shashemene Road Maintenance District seeks to buy 2-meter 48" concrete pipes for road maintenance and construction services via open tender. Bidders must submit a renewed business license, registration certificate, VAT certificate, tax payer certificate, and tax clearance.
