Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
  • Address , Phone: +251911984467
  • Website
  • Deadline13 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional)
  • opening dateጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories Consultancy Service

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት የምክር አገልግሎት ግዥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መስፈርት (TOR) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


የምክር አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/02/2019

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት የምክር አገልግሎት ግዥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መስፈርት (TOR) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመከፈላችሁ ማስረጃ፣የቫት ተመዝጋቢ፣ ቲን፣ በEGP የአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ ስለመሆኑ ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡ እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ጉምሩክ ከባቡር መነሻ ፊት ለፊት በሚገኘው አዋሽ ባንክ በኩል ወደ ውስጥ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 306 ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋጋ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል ፡፡ ጨረታው ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል ፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ+251911984467 ወይም +251910567578
ፋክስ 0114-421312
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Agricultural Works Corporation seeks consultancy services per the tender document's Terms of Reference. Eligible bidders must hold a relevant trade license, tax payment proof, VAT registration, TIN, and EGP supplier registration, and provide a tax clearance.
Save Tender