Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 166 ኪ.ሜ በኮይሻ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910692839
  • Website
  • Deadline20 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1,000.00 (አንድ ሺ ብር)
  • Bid Security500,000.00 (አምስት መቶ ሺ ብር)
  • opening dateበዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት
  • Categories Building Construction

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ በኮይሻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የድንገተኛ መታከሚያ አንድ ብሎክ ህንፃ ግንባታ (BC-5/GC-5 እና ከዚያ በላይ) አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለኮንታ ኮይሻ ወረዳ አስ/ር ጽ/ቤት በኮይሻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድንገተኛ መታከሚያ አንድ ብሎክ ህንፃ ግንባታ በ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመገንባት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡-

  1. በግንባታው ዘርፍ ደረጃ አምስት (BC-5/GC5) እና ከዚያ በላይ የተመዘገበ፣
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  4. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና በዘመኑ የታደሰ የግንባታ ስራ ፍቃድ፣
  5. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣
  6. የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ከግብር ዕዳ ነፃ የሚል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፣
  7. በመንግስት ግዥ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣
  8. የመልካም ስራ አፈፃፀም የ2015፣ የ2016፣ የ2017፣የ2018 ዓ/ም ውስጥ ሶስት እና ከዛ በላይ ማቅረብ የሚችል፣
  9. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በCPO ከታወቀ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
  10. ተጫራቾች የጨረታ ዶክምንት የማይመለስ 1,000 (አንድ ሺህ) ብር ብቻ በመክፍል ከኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር G+003 መውሰድ ይኖርባቸዋል፣
  11. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታ ዶክመንት በመግዛትና በዋጋ ማቅረብያ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናል 1፣ ቴክኒካል ኮፒ 1፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል 1፣ እና ፋይናንሻል ኮፒ 2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው ከላይ በተባለው 21ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
  13. በጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች የመወዳደርያ ነጥቦች (መስፈርቶች) በጨረታ ዶክመንቱ ላይ በጥንቃቄ ተግባራዊ ይደረጋል፣
  14. በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደርያ ነጥቦቹን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ቴክኒካል ግምገማ ያልፋሉ፣
  15. ተጫራቾች በጨረታ ዶክመንቱ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ሃሳቦች ከተገኙ የጨረታ መከፈቻ ቀን ከመድረሱ ሦስት ቀናት አስቀድሞ በአካል ወይም ከታች በተመለከተው ስልክ በመደወል ማስመዝገብ ይጠበቅበታል፡፡
  16. 5% ወደ ላይ እና ወደ ታች የአርትመቲክ ስህተት ተግባራዊ/ውድቅ ይደረጋል፡፡
  17. መስርያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0910692839/0917007585

አድራሻ፡- በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 166 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በኮይሻ ከተማ ይገኛል፡፡

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Construction of a one-block emergency treatment building at Koyisha Primary Hospital for Konta Koyisha Woreda. Open to contractors with BC-5/GC-5 or above, valid trade and construction licenses, TIN, VAT registration, tax clearance, supplier certificate, and good performance records.
Save Tender