መድሃኒቶችና ሰፕላይ እና ሬኤጀንቶች፣ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣ የምግብ፣ የጽዳት፣ የፅህፈት እና ሌሎች እቃዎች ግዥ - የድል ጮራ ሆስፒታል
የድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ድ/ዳ/ድ/መ/ሆ/02/19
በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል ለህብረተሰብ ፋርማሲ እና ለኢትዮጵያ ፋርማሲ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም መድሃኒቶችና ሰፕላይ እና ሬኤጀንቶች ፣ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ፣ የምግብ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ የህትመት ስራዎች ፣ ጨርቃ ጨርቆች ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች ፣ አናፂ እቃዎች እና የመኪና ጎማዎችና ባትሪዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች:-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ለ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ ግብር የከፈሉበት እንዲሁም እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- ለመድሃኒት ከ EFDA የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No.) ያላቸውና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺ ብር ) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል በድል ጮራ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር A/2 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO) ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ9:30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ጠዋት 3:30 ሰዓትተዘግቶ ከቀኑ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር A/2 ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ 10% ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈረም አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በጨረታው አሸናፊነቱን ለመሰረዝ ከጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ፣ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል ስልክ ቁጥር 0252115693 / 0982540408 / 0901103211 / ፖስታ ሳጥን ቁጥር 177
በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል
✨ messages.ai_summary
Dil Chora Hospital seeks eligible bidders to supply pharmaceuticals, supplies and reagents, medical equipment, food, cleaning, stationery, printing, textiles, electrical, plumbing, and vehicle tires and batteries. Bidders need a valid business license, tax clearance, VAT registration, TIN, EFDA license for medicines, and government procurement registration.
