አልባሳት፣ የቢሮ የፅሕፈት መሳሪያዎች፣ የህሙማን ቀለቦች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የማሽነሪና የጀኔሬተር ጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች ግዢ - የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
በሀገር መከለከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መ/ቁጥር .. ምዕ/ግ/ጨ/A-01/19
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በዳንሻ እና ኑቅምት ከተማ ውስጥ በሚገኙ ግምጃ ቤቶች ውስጥ የሚራገፉ የተለያዩ አይነት :-
- ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ አልባሳት እና ጫማዎች፤
- ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ አላቂ የቢሮ የፅሕፈት መሳሪያዎች፤
- ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ የትምህርትና ስልጠና መርጃ ዕቃዎች፤
- ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ የህሙማን ቀለቦች፤
- ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፤
- ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ የቅስቀሳ እና ፕሮፓጋንዳ ዕቃዎች
- ዳንሻ ከተማ የሚራገፉ የማሽነሪና የጀኔሬተር ጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች፤
- ኑቅምት ከተማ የሚራገፉ አላቂ የቢሮ የፅሕፈት መሳሪያዎች ሲሆን፤
ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በ1ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች :-
- አግባብ ያለው በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤
- የቫት ሰርተፍኬት፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን ማስረጃ ፤
- በጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
- በንግድ ስያሜው መሰረት የተዘጋጀና የተረጋገጠ 15 ቀን ያልሞላው የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ የሚችል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ (2%):- ከባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፤
የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በካሽ ዳንሻ በሚገኘው የምዕ/ዕዝ ግዥ ቢሮ በመምጣት ወይም በኢ/ያ ን/ባንክ አካውንት ቁጥር 1000478536945 በwestern command HQ ስም በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመስከረም 21/01/2019 ዓ/ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ::
የጨረታ ማስረከቢያ (CPO) መጠን
| 1) አልባሳት እና ጫማዎች | 11,990.18 |
| 2) አላቂ የቢሮ የፅሕፈት መሳሪያዎች፤ | 50,874.87 |
| 3) የትምህርትና ስልጠና መርጃ ዕቃዎች | 23,691.00 |
| 4) የህሙማን ቀለቦች | 143,711.19 |
| 5) አላቂ የፅዳት ዕቃዎች | 135,140.92 |
| 6) የቅስቀሳ እና ፕሮፓጋንዳ ዕቃዎች፤ | 1,999.38 |
| 7) የማሽነሪና የጀኔሬተር ጥገና መለዋወጫዎች | 19,803.00 |
| 8) ኑቅምት የሚራገፉ የፅሕፈት መሳሪያዎች፤ | 12,765.00 |
- ጨረታው ሀሙስ ጥቅምት 05/02/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 3:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጨረታው ሀሙስ ጥቅምት 05/02/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዳንሻ ከተማ በሚገኘው የምዕራብ ዕዝ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል::
- ተጫራቾች የእንዱን ዕቃ ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረበውን ስፔስፊኬሽን በአግባቡ ማንበብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የእንዱን ዕቃ ዋጋ በራሳቸው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ የሚያቀርቡትን ዕቃዎች ብራንድ ስሪት ወይም የዕቃውን ጥራት ደረጃ በግልፅ ተሞልቶ ማህተም ተደርጎበት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው መቅረብ አለበት::
- ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ በጨረታ ሰነዱ ላይ በሞሉት የዕቃዎች ስሪት መሰረት የዕቃዎችን ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ አለባቸው::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ :- ስልክ 0576603275 0913631100 መደወል ይቻላል
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Supply of clothing, footwear, consumable office stationery, educational materials, patient bracelets, cleaning supplies, promotional items, and machinery/generator maintenance spare parts for delivery in Dansha and Nukhumt. Bidders need a valid trade license, VAT and TIN certificates, supplier registration, tax clearance, bank statement, and CPO.
